የዌልስ ልኡሉ ቻርልስ
(ለሚስቱ ታማኝ እንደነበር
ተጠይቆ የመለሰው)
ሙሽራ ማለት ከኋላዋ ደስተኛ የመሆን ጥሩ ተስፋዋን ጥላ የመጣች ማለት ናት፡፡
አምብሮስ ቢርስ
(አሜሪካዊ ፀሐፊና ጋዜጠኛ)
ባል መሆን የሙሉ ጊዜ ሥራ ነው፡፡ ለዚህ ነው ብዙዎቹ ባሎች የማይሳካላቸው ሙሉ ትኩረታቸውን ለባልነት መስጠት አይችሉም፡፡
አርኖልድ ቤኔት
(እንግሊዛዊ ፀሐፊ)
ባሎች እንደ እሳት ናቸው፤ ካልተከታተሏቸው ድርግም ብለው ይጠፋሉ፡፡
Zsa Zsa Gabor
(ትውልደ ሃንጋሪ አሜሪካዊ
የፊልም ተዋናይ)
ሴት እሷም መልሳ ካላፈቀረችው በቀር ያፈቀራትን ወንድ መናቋ አይቀርም፡፡
ኤልዛቤት ስቶዳርድ
(አሜሪካዊት ደራሲና ገጣሚ)
ፍቅር አልባ ጋብቻ ማለት ጋብቻ አልባ ፍቅር ማለት ነው፡፡
ኬኔት ክላርክ
(እንግሊዛዊ የጥበብ ታሪክ ምሁር)
የሴትን ልብ ለመምታት እርግጠኛው መንገድ ተንበርክኮ ማለም ነው፡፡
ዳግላስ ጄሮልድ
(እንግሊዛዊ ፀሐፌ ተውኔት)
የወሊድ መከላከያ ለሚጠቀሙ ጥንዶች ከህፃናት ማሳደጊያ ቤቶቼ ውስጥ ልጅ አልሰጣቸውም፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ፍቅር አይገባቸውም፡፡
ማዘር ቴሬዛ
(የአልባንያ ተወላጅና የሮማ
ካቶሊክ መነኩሴ)