Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Monday, 05 March 2012 14:27

የፍቅር ጥግ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

ታማኝ ባልነበርሽ ጊዜ እንኳን እወድሽ ነበር፡፡ ታማኝ ብትሆኚ ምን ላደርግ ነበር?

ዣን ባፕቲስት ራኪን

(ፈረንሳዊ ፀሐፌተውኔት)

ያለፍላጐት ታማኝ ከመሆን ይልቅ ጭርሱኑ ታማኝ አለመሆን ይሻላል፡፡

ብሪግቲ ባርዶት

(ፈረንሳዊት የፊልም ተዋናይትና

የእንስሳት መብት ተከራካሪ)

አዎ…ጋብቻው ተመልሶ ሊጠገን በማይችልበት ደረጃ እስከፈራረሰበት ጊዜ ድረስ ታማኝ ነበርኩ፡፡

የዌልስ ልኡሉ ቻርልስ

(ለሚስቱ ታማኝ እንደነበር

ተጠይቆ የመለሰው)

ሙሽራ ማለት ከኋላዋ ደስተኛ የመሆን ጥሩ ተስፋዋን ጥላ የመጣች ማለት ናት፡፡

አምብሮስ ቢርስ

(አሜሪካዊ ፀሐፊና ጋዜጠኛ)

ባል መሆን የሙሉ ጊዜ ሥራ ነው፡፡ ለዚህ ነው ብዙዎቹ ባሎች የማይሳካላቸው ሙሉ ትኩረታቸውን ለባልነት መስጠት አይችሉም፡፡

አርኖልድ ቤኔት

(እንግሊዛዊ ፀሐፊ)

ባሎች እንደ እሳት ናቸው፤ ካልተከታተሏቸው ድርግም ብለው ይጠፋሉ፡፡

Zsa Zsa Gabor

(ትውልደ ሃንጋሪ አሜሪካዊ

የፊልም ተዋናይ)

ሴት እሷም መልሳ ካላፈቀረችው በቀር ያፈቀራትን ወንድ መናቋ አይቀርም፡፡

ኤልዛቤት ስቶዳርድ

(አሜሪካዊት ደራሲና ገጣሚ)

ፍቅር አልባ ጋብቻ ማለት ጋብቻ አልባ ፍቅር ማለት ነው፡፡

ኬኔት ክላርክ

(እንግሊዛዊ የጥበብ ታሪክ ምሁር)

የሴትን ልብ ለመምታት እርግጠኛው መንገድ ተንበርክኮ ማለም ነው፡፡

ዳግላስ ጄሮልድ

(እንግሊዛዊ ፀሐፌ ተውኔት)

የወሊድ መከላከያ ለሚጠቀሙ ጥንዶች ከህፃናት ማሳደጊያ ቤቶቼ ውስጥ ልጅ አልሰጣቸውም፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ፍቅር አይገባቸውም፡፡

ማዘር ቴሬዛ

(የአልባንያ ተወላጅና የሮማ

ካቶሊክ መነኩሴ)

 

 

Read 6438 times Last modified on Monday, 05 March 2012 14:29