Monday, 05 March 2012 14:19

ከአዲስ መድሃኒት ፋብሪካ ተዘረፈ የተባለ መድሃኒት ደሴ ላይ ተያዘ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(1 Vote)

አዲስ አበባ ከሚገኘው “አዲስ መድሃኒት” ፋብሪካ በግለሰቦች ተዘርፎ የወጣ ነው የተባለ ግምቱ ከ1.5 ሚሊዬን ብር በላይ የሆነ የተለያዩ መድሃኒቶችን የያዘ እሽግ ካርቶን በደሴ ከተማ በህገወጥ መንገድ ሊከፋፈል በተከማቸበት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ፡፡   የፋብሪካው ባለቤቶች የተዘረፍነው ከ2 ሚ. ብር በላይ መድሃኒት ነው ብለዋል፡፡ የተዘረፈው መድሃኒት በቁጥጥር ስር የዋለው ንፅህናውና ምቾቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ መቀመጡ በፈጠረው ጥርጣሬ እንደሆነ ፖሊስ ገልጿል፡፡ አራት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ካርቶን የተለያዩ መድሃኒቶች የያዘውን እሽግ በከተማው ለማሰራጨትና ለማከፋፈል የሞከሩ አስራ አንድ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ፖሊስ በኤግዚቢትነት የያዘው መድሃኒት ጊዜው ያለፈበት ይሁን አይሁን በጤና ባለሞያዎች እንደሚጣራ ተገልጿል፡፡ የደሴ ፖሊስ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ምርመራ እያካሄደ ሲሆን የፋብሪካው ባለቤቶች የተዘረፍነው ከ2 ሚሊዬን ብር በላይ የሚያወጣ መድኃኒት ነው በማለት መድሃኒቱ በሌሎች ክልሎችም ተሰራጭቷል የሚል ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

 

Read 27482 times Last modified on Monday, 05 March 2012 14:21