Saturday, 25 February 2012 14:10

ሊቨርፑል ለዋንጫ ረሃቡ ካርሊንግ ካፕን አነጣጥሯል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(1 Vote)

በነገው የካርሊንግ ካፕ ፍፃሜ ሊቨርፑል ከካርዲፍ ሲቲ ሲገናኙ ያለፈውን 6 የውድድር ዘመን ያለዋንጫ የቆየው ሊቨርፑል ለድሉ ቅድሚያ ግምት ወሰደ፡፡ የአንፊልዱ ክለብ ለዋንጫ የደረሰው ቼልሲንና ማን ሲቲን ጥሎ በማለፉ ሲሆን ለተጋጣሚው ካርዲፍ ሲቲ ባለው ወቅታዊ አቋም ከባድ ተቀናቃኝ ያደርገዋል፡፡ ኬኒ ዳግሊሽ የሊቨርፑልን የአጥቂ መስመር በሱዋሬዝ፤ ካሮልና ቤላሚ ጥምረት ያሰልፋሉ መባሉም ለዋንጫው የሰጡትን ትኩረት አሳይቷል፡፡ ሊቨርፑል ነገ ካሸነፈ ዌልሳዊው ክሬግ ቤላሚ በእንግሊዝ እግር ኳስ የመጀመርያውን የዋንጫ ድል የሚያጣጥም ሲሆን ይህን ድል ባለፈው የውድድር ዘመን ከማን ሲቲ በውሰት ተዛውሮ የተጫወተበት ካርዲፍ ሲቲ ላይ ሊያሳካ መቻሉ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ካርዲፍ ሲቲ ከሊቨርፑል ጋር በተገናኘባቸው 29 ጨዋታዎች 18 በማሸነፍና ሁለት አቻ የመውጣት ታሪክ ያለው ነው፡፡ በካርሊንግ ካፕ 11 ፍፃሜዎች በመሰለፍ የከፍተኛ ተሳትፎ ታሪክ ያለው ሊቨርፑል በሰባቱ ዋንጫውን ተነጥቋል፡፡

 

 

 

Read 3637 times Last modified on Saturday, 25 February 2012 14:15