Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 25 February 2012 13:14

የፖለቲካ ጥግ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሃላፊነትህን ብቻ ተወጣ፤ ታሪክ ፍርዱን ይሰጥሃል፡፡

ሃሪ ኤስ ትሩማን

(የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩ)

የትም ቦታ የሚፈፀም ኢ-ፍትሃዊነት በሁሉም ቦታ ላለ ፍትሃዊነት አደጋ ነው፡፡

ማርቲን ሉተር ኪንግ

(አሜሪካዊ የሲቪል መብት እንቅስቃሴ መሪ)

ሁሉም ጦርነቶች ለመጀመሪያዎቹ 20 ቀናት የህዝብ ድጋፍ አላቸው፡፡

አርተር ሽልሲንገር ጄ.አር.

(አሜሪካዊ የታሪክ ምሁር)

በጦርነት ወቅት ማናቸውም ዓይነት መዘግየቶች አደጋ ያስከትላሉ፡፡

ጆን ድራይደን

(እንግሊዛዊ ገጣሚ፣ ፀሃፌ ተውኔትና ሃያሲ)

የቦዘ የወታደር ዓይን የተመለከተ ማንኛውም ሰው ጦርነት ውስጥ ከመግባቱ በፊት በቅጡ ያስባል፡፡

ልኡል ኦቶ ቮን ቢስማክ

(የጀርመን ቻንስለር የነበሩ)

አንድ ንፁህ ዜጋ ከሚሰቃይ አስር ወንጀለኞች ቢያመልጡ ይሻላል፡፡

ዊሊያም ብላክስቶን

የዳኛ ሃላፊነት ፍትህን መፈፀም ነው፡፡ የእሱ ተግባር ግን ማዘግየት ሆኗል፡፡

ዥን ዲላ ብሩዬር

(ፈረንሳዊ ወግ ፀሃፊና የግብረገብ መምህር)

የሰው ማንነት የሚፈተነው በደግና ምቹ ጊዜ አይደለም፤ በፈተናና በውጣ ውረድ ጊዜ ነው፡፡

ማርቲን ሉተር ኪንግ ጄአር.

(አሜሪካዊ የሲቪል መብት እንቅስቃሴ መሪ)

የህግ ከፍተኛው መገለጫ ደንብና ሥርዓት ሳይሆን ወህኒ ቤት ነው፡፡

ጆርጅ ጃክሰን

(አሜሪካዊ ፖለቲከኛና ፀሃፊ)

ቅጣት ለብቀላ አይደለም፡፡ ወንጀልን ለመቀነስና ወንጀለኛውን ለማስተማር እንጂ፡፡

ኤልዛቤት ፍራይ

(የእንግሊዝ ወህኒ ቤት ሃላፊ)

የእስር ቤት አንድ ቀን ከሺህ ዓመት ይረዝማል፡፡

የቬትናሞች አባባል

 

 

 

 

 

Read 3389 times Last modified on Saturday, 25 February 2012 13:20