Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Tuesday, 21 February 2012 14:43

የአንጋፋው ደሪሲ የስብሃት ገ/ እግዚአቢሄር የቀብር ሥነስርዓት ተፈፀመ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ፓትርያርኩ  ችሎታቸውን አደነቁ

በርካታ  አርቲስቶቸና የጥበብ አደናቂዎቸ ተገኘተዋል

ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ባለፈው እሁድ ለሰኞ አጥቢያ በ76 ዓመቱ ከዚሀ ዓለም በሞት የተለየው አንጋፋው ደራሲ ስብሃት ገ/ እግዚአብሄር   የቀብር ሰነስርዓቱ ተፈፅሞልየኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን  ፓትርያርኩ አቡን ጳውሎስን ጨምሮ በርካታ አርቲስቶችናየደራሲው ቤተሰቦች ጓደኞቹና አድናቂዎቹ በቀብር ሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙ ሲሆን፤ ደብተር የያዙ ተማሪዎች ከነዩኒፎርማቸው ተገኝተው ነበር፡፡

የደራሲ ስብሃት ችሎታውን አድንቀው የተናገሩት ፓትርያርኩ፤ ስብሃት የብዙዎችን ትኩረት መሳብ የቻሉትl ከሌሎቻችን የተለየ ሆነው ሳይሆን እግዚአብሔር የሰጣቸውን ሃብት በሥራ ለመግለፅ ፈቃደኛ በመሆናቸው ብቻ ነው ሲሉ ሌሎችም አርአያነታቸውን እንዲከተሉ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

በሺዎች የሚገመቱ የአገር ውስጥና በአብዛኛው የውጭ አገር መፃህፍትን እንዳነበበ የሚነገርለት ደራሲ ስብሃት በጋዜጦችና መፅሔቶች ላይ ሲያቀርባቸው ከነበሩ በርካታ መጣጥፎች በተጨማሪ አምስት ስድስት ሰባ፣ ትኩሳት፣ ሌቱም አይነጋልኝ 7ኛው መልአክ፣ እነሆ ጀግና እናድፍረትና ግልፅነት በሚንፀባረቁባቸው ሥራዎቹና ለየት ባለ የአፃፃፍ ስዕልቱ በርካታ ተካዮችና አድናቂዎችን ያተረፈው ስብሃት የራሱን የሕይወት ታሪክ ባይፅፍም በእሱ ሕይወትና ሙያ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ሁለት መፅሃፍ ታትሞለታል፡፡ በጋዜጠኛና ደራሲ ዘነበ ወላ የተዘጋጀውን ማስታወሻ ቀዳሚ ሲሆን ሁለተኛ ጋዜጣ በደራሲ አለማየሁ ገላጋይ ሕይወትና ክህሎት የተፃፈው በትግራይ ዞን ከአድዋ ከተማ አቅራቢያ በምትገኝ ራገባረር የምትባል መንደር ውስጥ መጋቢት 1928 ዓ.ም የተወለደው ስብሃት ወደ አዲስ አበባ የመጣው በልጅነት ዕድሜው ሲሆን የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ተከታትለዖ እንዳጠናቀቀ የመጀመሪያ ዲግሪውን በ1951ዕ.ም ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ እንዳገኘ የሕይወት ታሪኩ ይጠቁማል፡፡

በፍልስፍናና የተለያዩ ትምህርት ዘርፎችን በአሜሪካና በአውሮፓ የተከታተለው ደራሲው ወደ አገሩ በመመለስ መነን፣ የካቲት ለተባሉት መፅሔቶችና አዲስ ዘመን ኢትዮጰያ ሄራልድ ጋዜጦች ላይ በአዘጋጅነት እና በአምደኝነት እንደሰራ ተገልፃል፡፡ ስብሃት በግል መፅሔቶችና ጋዜጦች ላይ በርካታ መጣጥፎችን በማቅረብ የሚታወቅ ሲሆን በተላይ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ለረጅም ጊዜ በአምደኝነት ሰርቷል፡፡ እስካለፈው ቅዳሜ ድረስም የደራሲው ማራኪና ጥልቅ መጣጥፎች በጋዜጣው ላይ ተስተናግደዋል፡፡

በትናንተው ዕለት በተፈፀመው የቀብር ስነስርዓ ላይ የተነበበው የደራሲው የህይወት ታሪክ ማራኪና ኪነጥበባዊ ውበት የተላበሰ በሚል አድናቆት የተቸረው ሲሆን ሳይታሰብ በድንገት የቀረበው ያድናቆትና የውዳሴ  ግጥም ግን አንጋፋውን ደራሲ የስነፅሁፍ ሰው የማይመጥን ነው ሲሉ አንዳንድ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተችተዋል፡፡

ትናንት ተሲያት ከ10 ሰዓት ጀምሮ በቅድስት ካቴድራል ሥላሤ ቤተክርስቲያን በርካታ ሰዎች ተገኝተው የነበር ቢሆንም የቀብር ስነ ሥርዓቱ እስከ 11 ሰዓት ተኩል ሳይፈፃም በመዘግየቱ ከፊሉ ታዳሚ ስነ ሥርዓቱ ሳይጠናቀቅ ለመሄድ ተገዷል፡፡

የዕድሜውን ግማሽ ያህል ከብዕርና ከመፃህፍት ያልተለየው ስብሃት ታሞ ሆስፒታል እስከገባበት ድረስ ከፅሁፍ ስራው ሳይለይ እንደቆየ ለማወቅ ተችሏል፡፡ መምህር ጋዜጠኛ ደራሲ ስብሃት ገ/እግዚአብሔር የሁለት ወንድና የሶስት ሴቶች አባት ነበር፡፡

 

 

 

Read 17940 times Last modified on Tuesday, 21 February 2012 15:38

Follow us on twitter

Due to an error, potentially a timed-out connection to Twitter, this user's tweets are unable to be displayed.