Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 18 February 2012 10:20

የፍቅር ጥግ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

ጓደኝነት

ፈፅሞ ማብራርያ አትስጥ፡፡ ጓደኞችህ አይፈልጉትም፡፡ ጠላቶችህ አያምኑትም፡፡

ቪክቶር ግራይሰን

(የብሪቲሽ ፖለቲከኛ)

ዕጣፈንታ ዘመዶችህን ይመርጥልሃል፡፡ አንተ ጓደኞችህን ትመርጣለህ፡፡

ጃኪውስ ዴሊሌ

(ፈረንሳዊ ገጣሚና ቢሾፕ)

ገንዘብ ሊያስገባህ በማይችለው ቦታ ጓደኞችህና መልካም ሥነምግባርህ ይዘውህ ይገባሉ፡፡

 

 

ማርጋሬት ዎከር

(አሜሪካዊት ገጣሚ፣ ደራሲና ጋዜጠኛ)

አምሳያህ ያልሆነ ጓደኛ አትያዝ፡፡

ኮንፊሽየስ

(ቻይናዊ ፈላስፋ፣ አስተዳዳሪና

የግብረገብ ሰባኪ)

ልብህ ድረስ ዘልቆ የሚገባ ጉዳት ለማድረስ ጓደኛህና ጠላትህ በጋራ መስራት አለባቸው፡፡ አንደኛው ስምህን ለማጥፋት፣ ሌላኛው ወሬውን ላንተ ለማድረስ፡፡

ማርክ ትዌይን

(አሜሪካዊ ፀሃፊና ተረበኛ)

መልካም ጐረቤት ትልቅ በረከት የሆነውን ያህል ክፉ ጐረቤት ክፉ ዕጣ ነው፡፡

ሔስዮድ

(ግሪካዊ ገጣሚ)

አወዛጋቢ ፍጡር ነኝ፤ ጓደኞቼ አንድም አይወዱኝም አሊያም ይጠሉኛል፡፡

ኦስካር ሌቫንት

(አሜሪካዊ ፒያኖ ተጫዋችና ተዋናይ)

የጥንት ጓደኞች ባጠቃላይ የብቸኛ ሰዎች መጠጊያዎች ናቸው፡፡

ማክስ ቢርቦህም

(የብሪቲሽ ወግ ፀሃፊ፣ ሃያሲና ካርቱኒስት)

ብቸኛ ሰዎች ብቻ ናቸው የጓደኝነትን ሙሉ ጣእም የሚያውቁት፡፡ ሌሎቹ ቤተሰብ አለላቸው - ለብቸኛና ለስደተኛ ግን ጓደኞቹ ሁሉም ነገሩ ናቸው፡፡

ዊላ ካተር

(አሜሪካዊ ደራሲ፣ ገጣሚና ጋዜጠኛ)

ጥሩ ሰው ከጓደኛው ጋር ያለው ግንኙነት ከራሱ ጋር እንዳለው ግንኙነት ነው፡፡

አሪስቶትል

(ግሪካዊ ፈላስፋ)

 

 

Read 5786 times Last modified on Saturday, 18 February 2012 10:24