Saturday, 18 February 2012 09:53

ዓለማችን ምርጥ አቀንቃኟን አጣች

Written by  ጥላሁን አክሊሉ
Rate this item
(0 votes)

የዊትኒ ሂውስተን ቀብር ዛሬ ይፈፀማል

ቤተሰቦቿ የቀድሞ ባለቤቷ በቀብሯ እንዳይገኝ ይፈልጋሉ

ከባለፈው እሁድ ጀምሮ የዓለም አቀፉን ሚዲያ ትኩረት የሳበው የታዋቂዋ የአር ኤንድ ቢ ሙዚቃ አቀንቃኝ የዊትኒ ሂውስተን ድንገተኛ ሞት ነበር፡፡ ዊትኒ ሂዊስተን በሎስአንጀለስ ከተማ በሚገኘው በቢቨርሊሂልስ ሂልተን ሆቴል በተከራየችው ክፍል የመታጠቢያ ገንዳ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በድን ሆና ያገኟት ፀጉር ሠሪዋ እና የግል ጠባቂዋ ነበሩ፡፡ ወዲያው የሆቴሉን አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ሰጪዎች ተሯሩጠው በመጥራት ትንፋሽዋን ለመመለስ ሙከራ አደረጉ፡፡ ግን ከሞት ሊያድኗት አልቻሉም፡፡

ዊትኒ ሂውስተን ከሌሊቱ 8 ሰዓት ከ55 ላይ መሞቷ በዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ይፋ ከመደረጉ 20 ደቂቃዎች ቀደም ብሎ አንዲት ወጣት በትዊተር ላይ ለዓለም ያሰራጨችው ሲሆን መረጃውን ያገኘችውም ከአቀንቃኟ ፀጉር ሰሪ ነበር፡፡ የቢቨርሊ ሂልስ የፖሊስ ባልደረባ የሆኑት ማርክ ሮዛን ለቢቢሲ በሰጡት ቃል፤ ከሆቴሉ የፀጥታ ሠራተኞች አስቸኳይ ጥሪ ደርሷቸው መሄዳቸውንና የዊትኒ አሟሟትን አስመልክቶ በሌላ አካል የተፈፀመ ወንጀል ስለመኖሩ ምንም መረጃ እንደሌለ ከገለፁ በኋላ ነገር ግን በአደንዛዥ እፅ ወይም በአልኮል ምክንያት የሞተች ከሆነ ውጤቱ ሊታወቅ የሚችለው ከስምንት ሳምንት በኋላ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

 

የእንግሊዙ “The Gaurdian” ጋዜጣ የዊትኒን ሞት ተከትሎ፤ “Whitney Houston US singer and Actress Dies Aged 48” በሚል ርዕስ ባቀረበው የዜና ዘገባ፣ የዊትኒ የረጅም ጊዜ የሙዚቃ አልበም አሳታሚ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ክሌቭ ዴቪስ የተናገረውን ጠቅሷል:- “ከዊትኒ ጋር ለረጅም ጊዜ ከመቆየቴ የተነሳ ለእኔ እጅግ ከባድ ሀዘን ነው” ብሏል - ዴቪስ፡፡ የጃዝ ሙዚቃ ኮከብ የሆነው ሄሪቢ ሀንኩክ በበኩሉ፤ “የዊትኒን ሞት ሰምቶ አለማዘን አይቻልም፡ምክንያቱም የእርሷ ህይወት መንፈስና ትንፋሽ በሁላችንም ውስጥ ስላለ የእርስዋ መሞት ብዙ ነገር አሳጥቶናል፡፡›› ሲል ተናግሯል፡፡የዊትኒ ቃል አቀባይ ስቲቭ ኤልዘር ደግሞ፤ ‹‹እርሷን ለምናውቃትና ለምንወዳት ሁሉ በጣም አስደንጋጭ ዜና ነው፡ አለማችን ተወዳዳሪ የሌላትን ዘፋኝ አጥታለች፡፡›› በማለት መናገሩን ጋዜጣው ጠቁሟል፡፡ ከማሪያ ኬሪ እስከ ክሪስቲና አጉሌራ ድረስ ያሉ በርካታ ድምጻዊን በጣም አስደማሚ ድምጽ እንዳት ያወሳው ጋዜጣው፤ ነገር ግን ዊትኒ ላይ ሊደርሱ እንደማይችሉ       አመልክቷል፡፡ “The New york Times” በበኩሉ የአKT‹” }e[p^m ÉUê vKu?ƒ ›[ð‹ ሲል ነው ዜናውን ያወጀው፡፡ ዋቂው ¾S<²=n ýaÇ=¿c` ስU*” ¢ዌM እንዲሁ፣ “¾ƒU xታ wትJ” ²?“¨<” ŸcTI SÅ”ÑØI ›Ãk`U፡፡ እርሷ የምንጊዜም ምርጥ አቀንቃኝ ነች፡፡ ይህን ዜና ስሰማ በእውነት፣ በእውነት በእውነት አስደንግጦኛል፡፡” ማለቱን ጋዜጣው አውስቷል፡፡ ዋሺንግተን ፖስት ደግሞ “Whitney  Houston Another lost soul?”  በሚል ርዕስ ባወጣው ሃተታ “ዛሬ በጣም አሳዛኝ ዜና ሰምተናል፡፡ ድምዊቷ ዊትኒ ሒውሰተን በሎስአንጀለስ ሆቴል ውስጥ ሞታ ተገኝታለች” ካለ በኋላ ከአደንዛዥ ሱስ ለመላቀቅ እየሱሰ ክርስቶስ እንዲረዳት ትፀልይ እንደነበር ጠቅሷል፡፡ ከመሞቷ በፊትም “አዎን እየሱስ ይወደኛል….” የሚል ዜማ ማዜሟን አስታውሷል፡፡

ከአሁን ቀደም በአደንዛዥ እጽ ሱስ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ እውቅ አርቲስቶች እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን ማርሊ ሞንሮ ፤ ጂሚ ሔንዲክስ ፤ ጀምስ ጆፕሊን፤ ጂሚ ሞሪስ፤ ኢልuስ ፕሪስሊ፤ ማይክል ጃክሰንና ኢሚ ዋይን ሃውስ ይጠቀሳሉ ፡፡

ዊትኒ ሂውስተን በመዝናኛ ኢንዱስትሪው ውስጥ የጎላ ድርሻ ከነበራቸው ከጆን ሩስል ሂውስተን እና የሀይማኖት መዝሙር አቀንቃኝ ከነበሩት እናቷ ሊሲ ሂውስተን በኒው ጀርሲ ግዛት እ.ኤ.አ ነሐሴ 19 ቀን 1964 ዓ.ም ነበር የተወለደችው፡፡

ዊትኒ ከልጅነቷ ጀምራ በብሉዝና በፖፕ እንዲሁም በሶል ሙዚቃ ስመጥር በሆኑት  በክርስትና እናቷ አሪታ ፍራንክሊን ታንፃ ነው ያደገችው፡፡ ከ11ዓመቷ ጀምራ በኒውጀርሲ ቤተክርስትያን መንፈሳዊ መዝሙሮችን ትዘምር ነበር፡፡ ከዘማሪነቷ ጎን ለጎን ከእናቷ ጋር ኒውዮርክ በሚገኝ የምሽት ክበብ ታቀነቅን የነበረ ሲሆን በወቅቱ በስራዋ ከተደነቀው የአሪስታ ሪከርድስ ባለቤት ክሌቭ ዴቪስ ጋር “ሆልድ ሚ” የተባለውን ነጠላ ዜማ ሰርታለች፡፡

በ1986 በራሷ ስም “ዊትኒ ሂውስተን” የተባለውን አልበም ከለቀቀች በኋላ ወደ አድማጭ ጆሮ ባደረሰቻቸው “ሴቪንግ ማይ ላይፍ” እና “ሀው ዊል አይ ኖው” በተባሉት ዜማዎቿ በአለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅናን ተቀዳጀች፡፡ ኒውዮርክ ታይምስን ጨምሮ ታዋቂ መፅሄቶችና ጋዜጦች “የሳምንቱ ድንቅ አቀንቃኝ” በማለት ሰፊ ሽፋን ሰጥተው አሞካሹዋት፡፡ በርካታ የቴሌቭዥንና የሬድዮ ጣብያዎች ከጫፍ እስከ ጫፍ ዜማዋን እያቀረቡ ዝናዋ በአውሮፓ፣ በእስያ፣ በአፍሪካ፣ በአውስትራሊያ እና በላቲን አሜሪካ ተዳርሶ ከአለም ዕውቅ ሙዚቀኞች መካከል አንዷ ልትሆን በቃች፡፡ ይሄን ተከትሎም ዊትኒ 170 ሚሊዮን ቅጂ አልበሞች፣ ነጠላ ዜማዎችና ቪድዮ ክሊፖች ቸበቸበች፡፡

ሂውስተን በህይወት ዘመኗ 10 ሙሉ አልበሞችን የሠራች ሲሆን ሰባት የስቱድዮ አልበሞችንና ሦስት የምርጥ ዘፈኖቿን ስብሰብ ያወጣች ሲሆን በዓለም ዙርያ ባስመዘገበችው ከፍተኛ ሽያጭም የአልማዝ፣ የፕላቲኒየም እና የወርቅ ሰርተፍኬት ተሸልማለች፡፡ ዊትኒ ለአድማጭ ካበቃቻቸው አልበሞችዋ መካከል “ሐው ዊል አይ ኖው ዩ”፣ “ሴቪንግ ማይ ላይፍ” ፣ “ግሬት ላቭ ኦፍ ኦል”፣ “አይ ዋና ዳንስ ዊዝ ሰምባዲ”፣ “ሶ ኢሞሽናል”፣ “ብሮክን ኸርትስ” የተባሉት ዜማዎቿ በቢል ቦርድ የሽያጭ ደረጃ ሰንጠረዥ ለረጅም አመታት በቀዳሚነት  ዘልቀዋል፡፡ የአርቲስቷ ዕውቅና የጀመረው ከ1985 አንስቶ ነው - በቢል ቦርድ 200 አልበሞች የሙዚቃ ሰንጠረዥ የመሪነቱን ደረጃ ስትይዝ፡፡

የመጀመሪያ ፊልሟን “ዘ ቦዲ ጋርድ” በ1992 ዓ.ም ከሠራች በኋላ ለፊልሙ ማጀቢያ ያቀነቀነችው ሙዚቃ በ94 ዓ.ም የግራሚ አዋርድን ሲያሸንፍ “አይ ዊል ኦልዌይስ ላቭ ዩ” የተባለው ነጠላ ዜማዋ በሴት አርቲስቶች ከተሰሩ ዜማዎች በአልበም ሽያጭ ቀዳሚ ሆኖ ነበር - በአንድ ሳምንት በሚሊዮን ኮፒዎች በመሸጥ፡፡

ዊትኒ በተለያዩ ፊልሞች ላይ ተውናለች፡፡ “ዌይቲንግ ቱ ኤክሴል ” እና “ዘ ፕሪቸርስ” በተሰኙት ላይ በመሪ ተዋናይነት የተወነች ሲሆን “ዘ ፕሪቸርስ” ላይ ለማጀቢያ ሙዚቃነት ያቀነቀነችው ዜማ በመንፈሳዊ ሙዚቃ ዘርፍ ከወጡት ሁሉ እስካሁን በሽያጭ ከፍተኛውን ሪከርድ እንደያዘ ነው፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ ዝናን ካጐናፀፏት ሥራዎች መካከል እ.ኤ.አ በ1984 ያቀነቀነችው “ማይ ላቭ ኢዝ ዩር ላቭ”፣ “ጀስት ዊትኒ” እና “ዋን ዊሽ” እንዲሁም፣ የ2003ቱ “ዘ ሆሊዴይ አልበም”፣ የ2004ቱ “አይሉክ ቱ ዩ” በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በሙዚቃ ስራዎቿ ባገኘቻቸው ሽልማቶች ብዛት በ2002 ዓ.ም ”ጊነስ ወርልድ ሪከርድስ” የተባለው የዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ከሴት ታዋቂ አቀንቃኞች የላቀች የምንግዜም ተሸላሚ በሚል ስሟን በመዝገቡ ውስጥ አስፍሯታል፡፡ ዊትኒ ጊነስ ውስጥ ለመስፈር የበቃችው ሁለት ጊዜ የግራሚ አዋርድስ ፣30 ጊዜ የሙዚቃ ቢል ቦርድ ፣ 22 ጊዜ የአሜሪካ የሙዚቃ አዋርድን ጨምሮ በአጠቃላይ 415 ሽልማቶችን በመሰብሰቧ ነበር፡፡

በ1980ዎቹ ከአሜሪካዊው የእግር ኳስ ተጫዋች ሬንደል ካኒንግህምና ከፊልም ተዋናዩ ከኤዲ መርፊ ጋር ሚስጥራዊ የፍቅር ግንኙነት እንደጀመረች ሲናፈስባት የነበረውን ወሬ እያስተባበለች የቆየችው ሂውስተን፤ የአር ኤንድ ቢ አቀንቃኝ ከሆነው ቦቢ ብራውን ጋር የፍቅር ግንኙነት መጀመሯን ያወጀች ሲሆን በ1992 ዓ.ም በጋብቻ ተሳስራ ቦቢ ክርስቲና የተባለች ሴት ልጅ ወለደች፡፡ እንግዲህ ከዚህ አመት ጀምሮ ነው የዊትኒ ሕይወት አቅጣጫውን የሳተው፡፡ ከቀጠሮ መቅረት፣ ኮንሰርቶችን መሰረዝ፣ ኮንሰርት አቋርጦ መውጣት፣ ከስራዋ መቅረት ክብደቷ እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ የሆሊውድ ጋዜጦች አደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚ መሆኗን የሚጠቁሙ ዘገባዎችና የፎቶ ማስረጃዎችን ማውጣት ጀመሩ፡፡

ለዚህ ሱስ የዳረጋት ባለቤቷ ቦቢ ብራውን ዊትኒ መሆኑን በኦፕራ ዊንፍሬይ ቶክ ሾው ላይ ቀርባ ባደረገችው ቃለምልልስ በይፋ የተናገረች ሲሆን ጥር 11 ቀን 2000 ዓ.ም በአውሮፕላን ማረፊያ፣  በባልና ሚስቱ ሻንጣ ውስጥ ማሪዋና የተባለው አደንዛዥ ዕፅ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተዘግቧል፡፡

ዊትኒ “በጥፊ ይመታኛል፣ ይተፋብኛል” በሚል ስትወነጅለው ከነበረው ባሏ ከቦቢ ብራውን ጋር የመሰረተችው ትዳር ከ15 አመት በኋላ በ2002 ዓ.ም ነበር በፍቺ የተቋጨው፡፡

ምንም እንኳን ከባሏ ከተፋታች በኋላ ከዕፅ ሱስ ለመውጣት ተከታታይ ህክምናዎችን ብትወስድም በድብቅ ዕፅ መውሰድ መቀጠሏን የሚያመለክቱ መረጃዎች መውጣታቸው አልቀረም፡ ከዚህ በኋላ ነገሮች እየተባባሱ መጡ፡፡ በአብዛኛዎቹ ኮንሰርቶች ድምፅዋ እየተበላሸ ሙዚቃዋን አቋርጣ ለመውጣት የተገደደችው አቀንቃኟ፤ በዚህም ለ25 አመታት የገነባችው ዝና እየደበዘዘ መጣ፡መጨረሻዋም አላማረም፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት በሆቴል ክፍሏ የመታጠቢያ ገንዳ ውስጥ ድንገት ሞታ ተገኘች፡፡

የዊትኒ ሂውስተን ዕረፍት እንደተሰማ የወሰደቻቸው አደንዛዥ ዕፅና አልኮል ቅልቅል መርዘዋት ሊሆን እንደሚችል ሲነገር የነበረ ቢሆንም ሀኪሞች የአሟሟቷን መንስዔ አረጋግጦ ለማወቅ እስከ ሁለት ወር ሊወስድ ይችላል ብለዋል፡፡ ይሁንና ለሞቷ መንስኤ ሆኗል በሚል በግንባር ቀደምትነት እየተወገዘ የሚገኘው የቀድሞ ባለቤቷ ቦቢ ብራውን ነው - በተይ በዊትኒ ቤተሰቦች ዘንድ፡፡ የ18 አመት ልጇ ቦቢ ክሪስቲና የእናቷን ድንገተኛ ሞት እንደሰማች በድንጋጤ ታማ ሆስፒታል ገብታለች፡፡

ከአቀንቃኟ ዜና ዕረፍት በኋላ የአለማችን ስመጥር አርቲስቶች ድንገተኛ የሞት ዜናዋ እንዳስደነገጣቸው በተለያዩ ሚዲያዎች ገልፀዋል፡፡ ከእነዚህ አርቲስቶች መካከል ቢዮንሴ አንዷ ስትሆን “የዊትኒ ድንገተኛ ሞት የሚያንገበግብ ነው” ስትል ሃዘኗን ገልፃለች፡ ክሪስቲና አጉሌራ በበኩሏ “በዓለማችን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ላይ ጥቁር ጥላ አጥልቷል“ ያለች ሲሆን ታዋቂዋ የሶል ሙዚቃ አቀንቃኝ እና የዊትኒ የቅርብ ዘመድ የሆነችው አሪታ ፍራንክሊን “ቤቴ ሆኜ በቲቪ በሰበር ዜና ላይ መሞቷን ስሰማ ማመን ተስኖኝ ወደ ቴሌቨዥኑ ስክሪን ተጠግቼ ደጋግሜ የተጻፈውን ማንበብ ጀመርኩ“ ብላለች፡፡ “የጓደኛዬን ሞት ስሰማ በእንባ ታጠብኩ፤ ለቤተሰቦችዋና በአለም ላይ ላሉት አፍቃሪዎችዋ መፅናናትን እንዲሰጣቸው ፀለይኩ” ያለችው ደግሞ ማሪያ ኬሪ ናት፡፡

ዛሬ በሚካሄደው የቀብር ስነስርአቷ ላይ በመላው አሜሪካ የሚገኙ በርካታ ዝነኛ አርቲስቶችና ዕውቅ ሰዎች እንዲሁም አፍቃሪዎቿና አድናቂዎቿ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ የቀድሞ ባለቤቷ ቦቢ ብራውን በቀብር ስነስርዓቱ ላይ እንደሚገኝ የተገለጸ ቢሆንም የዊትኒ ቤተሰቦች ግን ቀብሩ ላይ እንዳይገኝ ተቋውሞ እያሰሙ ነው፡፡ አርቲስቷ ከ18ሺ ሰው በላይ በሚያስተናግድ አዳራሽ ውስጥ ስንብት እንደሚደረግላት ተገልጿል፡፡

 

 

Read 15712 times Last modified on Saturday, 18 February 2012 12:46