Saturday, 11 February 2012 11:01

በቀዮቹ ፍጥጫ ፀብ እንዳይፈጠር ተሰግቷል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

በፕሪሚዬር ሊግ ታሪክ እኩል 19 ግዜ ሻምፒዮን በመሆን ከፍተኛውን የውጤት ክብረወሰን ያያዙት ማን ዩናይትድ እና ሊቨርፑል ዛሬ በኦልድትራፎርድ ሲገናኙ የኤቭራና ሱዋሬዝ ፀብ እንዳያገረሽ ተሰጋ፡፡ አሰልጣኝ ኬን ዳግሊሽ ከቅጣቱ በኋላ ለሱዋሬዝ ድጋፋቸውን ሲገልፁ ፈርጊ በበኩላቸው ፀቡ በዛሬው የኦልድትራፎርድ ጨዋታ ዳግም ያጋጥማል ብለው እንደማያስቡ ተናግረዋል፡፡ በኦልድትራፎርድ ለኡራጋዊው ስዋሬዝ መልካም አቀባበል ላይኖር እንደሚችል የሰጉ ዘገባዎች ሁኔታው የሁለቱን ቡድኖች ፍጥጫ እንደሚያከረው እየገለፁ ናቸው፡፡

ሁለቱ ክለቦች ከወር በፊት በኤፍ ኤካፕ 4ኛ ዙር ጨዋታ ላይ በተገናኙበት ወቅት ሊቨርፑል 2ለ1 ማን ዩናይትድን ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡ ፈርጉሰን በዛሬው ጨዋታ ሊቨርፑልን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ለአንድ ቀን እንኳን ለመያዝ ሲያተኩሩ ዳግሊቭ በበኩላቸው የቀጣይ ዓመት የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎአቸውን ለማጠናከር ያቅዳሉ፡፡ በኦልድትራፎርድ የሚገኝ ድልን በማን ሲቲ ላይ ጫና ይፈጥራል ብለው እንደሚያምኑ የሚናገሩት ፈርጉሠን ሊቨርፑል ከዋንጫ ፉክክር ውጭ ነው ብለዋል፡፡ ሉዊስ ስዋሬዝ  በኤፍኤካፕ የአራተኛ ዙር ጨዋታ በአንፊልድ ከኤቭራ ጋር በፈጠረው ግጭትና ተሳድቧል ተብሎ ጥፋተኛ በመደረጉ የ8 ጨዋታ ቅጣት ተጥሎበት መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በፕሪሚዬር ሊጉና በሌሎች ውድድሮች በተደረጉ ያለፉት 15 ጨዋታዎች ማንዩናይትድ 2 ሲሸነፍ ሊቨርፑል ደግሞ ሶስቴ ሽንፈት ገጥሞታል፡፡ ሁለቱ ክለቦችበመጀመሪያ ዙር የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታ ኦንፊልድ ላይ ሲገናኙ 1ለ1 አቻ ወጥተዋል፡፡

 

 

 

Read 2267 times Last modified on Saturday, 11 February 2012 11:09