Saturday, 07 November 2015 09:06

ቅዱስ ሲኖዶስ ያለፈቃድ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም በሚዲያ የሚያስተምሩትን በሕግ እጠይቃለሁ አለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

   ቤተ ክርስቲያኒቱ በማታውቀው ሁኔታ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ፈቃድ ሳያገኙ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ትምህርታዊ ስብከት የሚያስተላልፉ፤ ዝማሬ የሚያሰሙ፤ ጻሕፍት፣ መጽሔቶች፣ ጋዜጦችና ልዩ ልዩ በራሪ
ወረቀቶችን የሚያሳትሙ በአገሪቱ ሕግ እንዲጠየቁ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን፤ የሚመለከታቸው የሚዲያ አካላትም ማሳሰቢያ እንዲደርሳቸው ይደረጋል፤ ብሏል፡፡
ሲኖዶሱ ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2008 ዓ.ም ለ12 ቀናት ሲያካሒድ የቆየውን መደበኛ ስብሰባ ሲያጠናቅቅ፣ 20 ነጥቦች ያሉት መግለጫ ያወጣ ሲሆን ከሚዲያ ጋር በተገናኘ ሁለት ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
የመጀመሪያው፣ ያለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ፈቃድ በስሟ ትምህርታዊ ስብከት ሲያስተላልፉና ዝማሬ የሚያሰሙ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ያሳለፈው ውሳኔ ሲሆን፤ መግለጫው እኒህን አካላት ለይቶ ባይጠቅሳቸው ምልዓተ ጉባኤው በተወያየበት ወቅት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሃይማኖታዊ ዝግጅት የሚያቀርቡ አካላት በስም መነሳታቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ የቴሌቪዥኑ የፕሮግራሚንግ ኮሚቴ ከጣቢያው ጋር ውል ገብተው በሳምንት አንድ ጊዜ ሃይማኖታዊ ትምህርት ለሚያቀርቡት ለማኅበረ
ቅዱሳን፣ ለቃለ ዐዋዲ፣ ለታዖሎጎስ እና ለኤንሼንት ዊዝደም ፕሮግራም ክፍሎች አገልግሎታቸውን የሚደግፍ የታደሰ ፈቃድ ወይም ደብዳቤ ከሚመለከተው የመንግስትም ሆነ የሃይማኖት አካል እንዲያስገቡ አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

Read 1471 times