Saturday, 07 November 2015 09:06

የጃፓን መንግስት የጠ/ሚ አማካሪ ንዋይ ገ/አብን ሊሸልም ነው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

የኢትዮጵያና የጃፓንን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት አጠናክረዋል ያለቻቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ነዋይ
ገ/አብን የጃፓን መንግስት የሀገሪቱን ትልቁን የክብር ሽልማት እንደሚያበረክትላቸው ተገለፀ፡፡
ሽልማቱ በቅርቡ በአዲስ አበባ በሚከናወን ስነስርአት ለተሸላሚው እንደሚበረከትላቸው የጠቆመው በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ፤
የክብር ሽልማቱ በጃፓን መንግስት በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝና ለታዋቂ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች የጦር አዛዦች የሚሰጥ የክብር ሽልማት መሆኑን ገልጿል፡፡
“ኦርደር ኦፍ ዘ ራይዚንግ ሰን ጐልደን ሲልቨር” የተሰኘው ሽልማት የሚበረከትላቸው አማካሪው፤ ላለፉት 6 አመታት የኢትዮ ጃፓንን የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ምክክር ሲመሩ  ሚናቸው የላቀ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡
አቶ ንዋይ ገ/አብ ላለፉት 19 አመታት የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊና የጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሣለኝ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ በመሆን እየሠሩ ይገኛሉ፡፡

Read 1496 times