ጥሬ ስጋን ጨምሮ በአገሪቱ የሚገኙ የባህል ምግብና መጠጦችን በስፋት የሚያስተዋውቅ “በጥቅምት አንድ አጥንት” የተሰኘ የምግብና የመጠጥ ፌስቲቫል ዛሬ በኤግዚቢሽን ማዕከል ይከፈታል፡፡
ሴንቸሪ ፕሮሞሽን ሰርቪስ፤ ከቢጂ አይ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደው ይኸው የምግብና የመጠጥ ፌስቲቫል፤ የአገሪቱን የባህል ምግቦችና መጠጦች በማስተዋወቅ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ የፕሮግራሙ አዘጋጆች ገልፀዋል፡፡ ፌስቲቫሉ እስከ ነገ ጥቅምት 14 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ ይቆያል፡፡