Saturday, 10 October 2015 15:55

ኢ.ቢ.ኤስ: ሃይማኖታዊ የቲቪ ፕሮግራሞች የታደሰ ፈቃድ እንዲያስገቡ አዘዘ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(11 votes)

     የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ፤ በሳምንት አንድ ቀን በጣቢያው መንፈሳዊ ዝግጅት  የሚያስተላልፉ ሃይማኖታዊ ፕሮግራሞች፣ የታደሰ ፈቃድ በአስቸኳይ እንዲያስገቡ አዘዘ፡፡ የጣቢያ ፕሮግራሚንግ ኮሚቴ መስከረም 21 ቀን 2008 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ፤ ማኅበረ ቅዱሳን፣ ቃለ ዐዋዲ፣ ታዖሎጐስ እና ኤንሼንት ዊዝደም የተባሉ አራት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ከሚመለከተው የመንግሥትም ሆነ የሃይማኖት አካል ለመስበክ ያስፈቀዱበትን ወይም እያደረጉ ያሉትን አገልግሎት የሚደግፍ የታደሰ ፈቃድ ወይም ደብዳቤ በአስቸኳይ እንዲያስገቡ ጠይቋል፡፡ባለፈው ሳምንት እትማችን፣ “በታዖሎጐስና ቃለ ዐዋዲ የኢቢኤስ ፕሮግራሞች ላይ ተቃውሞ ተነሳ” በሚል ርዕስ ፕሮግራሞቹ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ክብርና አስተምህሮ የሚጋፉ በመሆናቸው በስሟ እንዳይጠቀሙ የሚቀሰቅስ የድጋፍ ፊርማ በመሰብሰብ ላይ መሆኑን  መዘገባችን ይታወሳል፡፡
በሌላ በኩል  የተጠቀሱት ሃይማኖታዊ ፕሮግራሞች አዘጋጆች፣ በወጣው ዘገባ ላይ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡

Read 3551 times