Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 04 February 2012 12:15

የፖለቲካ ጥግ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

“ጦርነት የፖለቲካ ቅጥያ ነው፡፡” በዚህ መንፈስ ጦርነት ፖለቲካ ነው፤ ጦርነት ራሱም ፖለቲካዊ እርምጃ ነው፡፡

ማኦ ዚዶንግ

(ቻይናዊየፖለቲካ ባለስልጣን)

ክፉ ዓላማ ሁሌም በክፉ መንገዶችና በክፉ ሰዎች መደገፉ አይቀርም፡፡

ቶማስ ፔይን

(አንግሎ አሜሪካዊ የፖለቲካ ፈላስፋ)

ለፖለቲካ አንድ ሳምንት ረዥም ጊዜ ነው፡፡

ሃሮልድ ዊልሰን

(የብሪቲሽ ጠ/ሚኒስትር የነበሩ)

አጋር ልክ እንደጠላት በአይነ ቁራኛ መጠበቅ አለበት፡፡

ሊዮን ትሮትስኪ

(የሩሲያ አብዮታዊ መሪ)

አንድ እንግሊዛዊ ሱሪ ሊኖረው እንደሚገባ ሁሉ ፓርቲም ሊኖረው ይገባል፡፡

በርትራንድ ረስል

(የብሪቲሽ ፈላስፋና የሂሳብ ሊቅ)

ሰማይ ለወረደው ዝናብ ምስጋናውን የወሰደ የትኛውም ፓርቲ፤ ተፎካካሪዎች ለድርቁ ተጠያቂ ቢያደርጉት መገረም የለበትም፡፡

ድዋይት ዊትኒ ሞሮው

(አሜሪካዊ ዲፕሎማትና ፖለቲከኛ)

የፓርቲዎቹ መሪዎች የገዛ ራሳቸውን ውሸት እንዳያምኑ አስጠንቅቆዋቸዋል፡፡

ጆን አርቡትኖት

(ስኮትላንዳዊ ፀሃፊና ሃኪም)

እኔ ለፖለቲካ አልተፈጠርኩም፡፡ ምክንያቱም የተፎካካሪዬን ሞት ለመመኘት ወይም ለመቀበል አቅም የለኝም፡፡

አልበርት ካሙ

(ትውልደ - አልጀርያ ፈረንሳዊ ደራሲ፣ ወግ ፀሃፊና ፀሃፌ ተውኔት)

ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ይልቅ ገጣሚ መሆን እንደሚሻለኝ ሳውቅ ፖለቲካን ተውኩት፡፡

ጆን ፓርዶ

(እንግሊዛዊ ፖለቲከኛ)

በፖለቲካ ውስጥ ሆነህ ወደ አንድ ቢሮ ስትገባ ማናቸው እንደሚደግፉህና ማናቸው እንደሚቃወሙህ ካላወቅህ በተሳሳተ ሥራ ላይ ነህ፡፡

ሊንዶን ባይኔስ ጆንሰን

(የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩ)

 

 

Read 3860 times Last modified on Saturday, 04 February 2012 12:17