Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 28 January 2012 11:55

የፖለቲካ ጥግ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሰዎች የሚገልጿቸውን የተለያዩ አስተያየቶችና አመለካከቶች መፍራት የለብንም፡፡

ሱሃርቶ

(የኢንዶኔዢያ ከፍተኛ የፖለቲካ ባለሥልጣን)

ፕሬስን እኮ አልጠላም፡፡ ብዙው ነገራቸው ግን አይጥመኝም፡፡ እንደዚያ መሆን ከፈለጉ ግን… ልዑል ፊሊፕ (የንግስት ኤልዛቤት 2ኛዋ እንግሊዛዊ ባል)

የእንግሊዝ ጋዜጠኝነት በትንሽዬ የአልኮል መጠጥ ጉዳት አይደርስበትም፡፡

ሩፐርት ሙድሮክ

(ትውልደ አውስትራሊያ - አሜሪካዊ የሚዲያ ኢንተርፕርነር)

(“The Times” ጋዜጣ ቢሮ ባለበት ኢስት ለንደን መጠጥ ቤት አለመኖሩን ለመጠቆም የተናገረው)

ጋዜጠኝነት - ባዶ ቦታን የመሙላት ፈተናን የመወጣት ችሎታ ነው!

ሬቤካ ዌስት

(ትውልደ አይሪሽ- እንግሊዛዊ ደራሲ፣

ሃያሲና ጋዜጠኛ)

የአንድ አገር ጋዜጦች በበጐ ዜናዎች ከተሞሉ፣ ወህኒ ቤቶቹም በበጐ ሰዎች ይሞላሉ፡፡

ዳንኤል ፓትሪክ ሞይኒሃን

(አሜሪካዊ ምሁርና ፖለቲከኛ)

ዘመናዊ ጋዜጠኝነትን በመወገን ብዙ ሊባልለት ይችላል፡፡ ያልተማሩ ሰዎችን አስተያየት እያመጣልን ከማህበረሰቡ ድንቁርና እንዳንርቅ ያደርገናል፡፡

ኦስካር ዋይልድ

(አይሪሽ ገጣሚ፣ ፀሐፌ ተውኔት እና ተረበኛ)

ውሻ ሰው ሲነክስ ዜና አይደለም፤ ነገር ግን ሰው ውሻ ሲነክስ ዜና ይሆናል፡፡

ጆን ቢ. ቦጋርት

(አሜሪካዊ ጋዜጠኛ)

ሁሉም ቀኑን ሙሉ ከሚፈስለት ብዙ መረጃ የተነሳ የተፈጥሮ አስተውሎቱን አጥቷል፡፡

ገርትሩድ ስቴይን

(አሜሪካዊ ፀሐፊ)

ሚዲያ የሚለው ቃል መጥፎ ጋዜጠኝነት እንደማለት ሆኗል፡፡

ግርሃም ግሪን

(እንግሊዛዊ የረዥም ልቦለድ ደራሲ)

ሚዲያ፤ የመንፈሳውያን ጉባኤ ይመስላል፡፡

ቶም ስቶፓርድ

(ትውልደ - ቼክ እንግሊዛዊ ፀሐፌ ተውኔትና የስክሪፕት ፀሐፊ)

 

 

Read 3637 times Last modified on Saturday, 28 January 2012 11:59