Tuesday, 26 May 2015 07:54

“ሰው ሁሉ እንደየሀጢያቱ ይጠበጠባል!”

Written by 
Rate this item
(13 votes)

ይህ ታሪክ በሩሲያ የተፈፀመ ታሪክ ነው፡፡ በአበሽኛ እንተርከዋለን …. በቀድሞው ዘመን አንድ የ80 ዓመት አዛውንት እሥር ቤት ይገባሉ አሉ፡፡ ከዚያም፤ ታሣሪው ሁሉ እንደሚሆነው ለምርመራ ተጠርተው፤ “ወንጀለኛ ነዎት ይመኑ!” ይባላሉ፡፡

“ወንጀለኛ አይደለሁም” ይላሉ አዛውንቱ፡፡

“ሌላ ነገር ሳይከተል ቢያምኑ ይሻልዎታል!” ይላል መርማሪው፤ በከባድ የማስፈራራት ድምፅ።

“ያልሆንኩትን ነኝ ብዬ አላምንልህም!” ይላሉ በቁርጠኝነት፡፡ መርማሪው በከፍተኛ ንዴት ማጅራታቸውን እያዳፋ ወደ ማረፊያው ክፍል ይወስዳቸውና ባልተወለደ አንጀቱ፣ የበላ የጠጣውን ያህል ይደበድባቸዋል፡፡ አዛውንቱ ደም በደም ይሆናሉ፡፡ እግራቸው መራመድ እስከሚያቅታቸው ደረስ ይተለተላል፡፡

በኋላም፤ ወደ እሥር ቤቱ አምጥተው ይወረውሯቸዋል፡፡ እሥር ቤት የተቀበላቸው አንድ ወጣት ወዳጃቸው፤

“አባቴ ምነው እንዲህ ጎዱዎት? እኛን ወጣቶቹን እንኳን እንዲህ አልደበደቡንም’ኮ?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡

አዛውንቱም የሚከተለውን ወግ ይነግሩታል፡፡

“በአንድ ወቅት የዐርብ ስቅለት ዕለት ፆመኛው ሁሉ ወደቤተስኪያን ሄዶ በሚሰግድበት ወቅት ለቄሱ በፆሙ ወቅት የተሳሳተውን ይናገራል፡፡ ወይም ይናዘዛል፡፡ ቄሱም በቄጤማ ቸብ እያደረጉ እንደስህተቱ መጠን የሚሰግደውን ቁጥር ይሰጣሉ፡፡ ሐጢያቱን ለማስተሰረይ፡፡

አንዱ - “በፆም ተሳስቼ በልቻለሁ” ይላቸዋል፡፡

ቄሱ - በቄጤማው ይመቱትና፤

“ሃያ ስገድ” ይሉታል፡፡

ሌላው - “አባቴ፤ ሰው ተሳድቤአለሁ” ይላል፡፡

ቄሱ - “ሰላሳ ስገድ” ይሉታል፡፡ ደሞ ሌላው ይመጣል፤

“አባቴ፤ በፆሙ ወቅት ከአልጋው ወድቄያለሁ ይላቸዋል” ቄሱም በቄጠማው መታ ያደርጉትና

“ስልሳ ስገድ!” ይሉታል፡፡

በመጨረሻ አንድ ፈርጠም ያለ ጎልማሳ ይመጣና ወደ ጆሮአቸው ጠጋ ብሎ፣ በዝቅተኛ ድምፅ፤

“አባቴ፤ ይቅር ይበሉኝ፤ ከሚስትዎ ጋር ተሳስቼ ተኝቻለሁ” ይላቸዋል፡፡

ቄሱም ከመቅፀበት የብረት መቋሚያቸውን ብድግ ያደርጉና አናቱን ይሉታል!!

ሰውዬም፤ “ምነው አባቴ! ሰውን ሁሉ በቄጤማ ሲጠበጥቡ እኔን በብረት መቋሚያ መቱኝ?” አላቸው፡፡

ቄሱም፤

 “ሰው ሁሉ እንደየሐጢያቱ ይጠበጠባል!” አሉት ይባላል፡፡

                                             *        *      *

ህዝብ የሚደግፈውንም ሆነ የሚቀጣውን ፓርቲ ያውቃል፡፡ ያም የልማታችንን ወይም የጥፋታችንን፤ የመታመናችንን አሊያም ተአማኒነት የማጣታችንን መጠን ያሳየናል፡፡ እነሆ፣ ምን ያህል ህዝብ ውስጥ የመግባታችንንና ምን ያህልም ልቡ ውስጥ እንዳደርን፤ ውጤታችንን በአንድ ጀንበር የሚወሰንበት ሰዓት ጋ ደርሰናል፡፡ የምርጫ ካርድ የህዝብ ኃይል ነው፡፡ የትኛውንም ፓርቲ በስሜት ሳይሆን በነቃ አዕምሮ የሚመርጥ ህዝብ የነገ ዕጣ ፈንታውን ዛሬ የወሰነ ነው፡፡ “ህዝቡ የፈለገውን ፓርቲ መምረጥ ካልቻለ ፓርቲው የፈለገውን ህዝብ ይምረጥ” ይላል ብሬሽት፡፡ የተዛባ የምርጫ ሁኔታን ሲጠቁመን ነው፡፡ ስለሆነም እንጠንቀቅ፡፡ ህዝብ የሚመርጠውን በልቡ ይዞ የሚኖር ነው፡፡ የልቡን በእጁ ካርድ ማሳየቱ አይቀርም፡፡ የበደልነው፣ ያጠፋነው ነገር ካለ በምጫው ይመሰክርብናል፡፡ ይቀጣናል፡፡ ጥፋት አጥፍተን የጥፋቱን ማርከሻ ይቅርታ መጠየቅ ወይንስ ሌላ ማምለጫ ዘዴ መፈለግ? ለሚለው ጥያቄ በየዘመኑ ያየነው በአብዛኛው ጥፋትን በጥፋት ለመሻር ሲሞከር አይተናል፡፡ ሳኦ ሳኦ የተባለ የቻይና መሪ በጥንት ጊዜ “ዓለም ከሚክደኝ ዓለምን ብክድ ይሻለኛል” በሚል መርህ አንዱን የጦር አዛዡን ገድሎ የሱ ጥፋት ነው ጦሬን ለዚህ ያበቃው፤ ብሏል ይባላል፡፡ ሰበብ ወይም ማምለጫ ዘዴ (Scapegoat) ለጊዜው እንጂ ለዘለቄታው አይበጅም፡፡ ይህን የተገነዘበ ህዝብ የታደለ ነው፡፡ ጨውን ከአሞሌ፣ ወመቴን ከአለሌ፣ ጨለሌን ከጮሌ የሚለይ ዐይን ሊኖር ይገባል፡፡ “አስመሳይ ተራማጅ” ይባል የነበረው በድሮው ጊዜ በዋዛ አይደለም፡፡ “ቁልቋል የወደቀው ቅርንጫፍ ሲያበዛ ነው” የሚለውን ተረት ልብ-ማለት ተገቢ ነው፡፡ ልንፈጥር የምንፈልገውን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንወቅ፡፡ እንመንበት፡፡ በተግባር እንደምናውለው እርግጠኛ እንሁን፡፡

“ዕውር አይናማ ተሸክሞ የምናይበት ሥርዓት አንፈልግም” ይሉ ነበር የግሪክ አበው፡፡ እኛም አንፈልግም፡፡ የሚመራን ዐይናማ መሆን አለበት፡፡ በእርግጠኝነት አገሩን የሚያይና የሚወድ መሆን አለበት፡፡ የተፃፈውን የሚያከብር መሪ ያሻናል፡፡ የተፃፈው መለወጥ ካለበት ደግሞ በግትርነት አይለወጥም የማይልና ለውጥንና መለወጥን የማይፈራ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከሁሉም በላይ በራስ መተማመንን የህልውናው መሠረት ያደረገ ሊሆን ይገባል፡፡

ከእስከዛሬው ምርጫ ትምህርት ያገኘን ከሆነ ከማናቸውም መጭበርበርና ማጭበርበር ነጻ እንወጣለን፡፡ ከታዛቢ አድልዎ እንድናለን፡፡ “ከላም አለኝ በሰማይ” የሥልጣን መቋመጥ፣ በዚያም ከሚፈጠር መተረማመስ እንገላገላለን፡፤ ዲሞክራሲ የልመና ድርጎ ይመስል ለእነገሌ ይሄን ያህል የፓርላም ወንበር፣ ለእነእገሌ ይሄን ያህል፤ እያልን ሻሞ ብለው ለራሳቸው እንደወሰዱት ሰው እንዳንሆን እንጠነቀቃለን፡፡ በመላው አፍሪካ ተከስቶ ስናይ እንደከረምነው ዓይነት ምርጫ፤ ብሶት የሚጉረመረምበት እንዳይሆን፣ ኖረን አልነበርንም የምንልበት እንዳንሆን፤ ብርቱ ጥረት እናደርጋለን፡፡

ምርጫ፤ መሰረታዊ የዲሞክራሲ ባህል ነው፡፡ “አረረም መረረም ማበሬን ተወጣሁ” ይላሉ አበው፡፡ ምርጫ በየአምስት ዓመቱ እየተሻለው እንዲመጣ እንመኝ፡፡ ለዓለም አቀፍ ፍጆታ (International Consumption) ብለን ሳይሆን ለራሳችን ህዝብ ፍጆታ እናስብ፡፡ መንገዳችን የሚቃናው ሁላችንም እንደምንሄድበት አድርገን መጥረግ ስንችል ነው፡፡ ለዚሁም ትምህርታችንን ይግለጥልን!

ከግል ጥቅማችን፣ ከፓርቲያችን ጥቅም ወይም ከሌላ ከማናቸውም ወገናዊ ጥቅም ውጪ አገራችንን ብቻ አስበን የምንጓዝ ከሆንን ምርጫ የተቀደሰ ይሆናል፡፡ ይህ ሳይሆን በተቃራኒው ሐጢያት የሠራንበት ሂደት ከሆነ፤ “ሰው ሁሉ እንደየሐጢያቱ ይጠበጠባል” የሚለው ብሒል ዛሬም ባይሆን ነገ በጭራሽ መድረሱ የማይቀር ሐቅ ይሆናል!  

Read 4034 times