ጄምስ ባልድዊን
(አሜሪካዊ ፀሐፊና የሲቪል መብት ተሟጋች)
ፍቅር ካከተመ በኋላ መፋቀራቸው የማያሳፍራቸው በጣም ጥቂት ሰዎች አሉ፡፡
ፍራንሶይስላ ሮቼፎካልድ
(ፈረንሳዊ የአባባሎች ፀሐፊና የሥነምግባር ሊቅ)
ሁለት ነፍሶች በአንድ፤ ሁለት ልቦች አንድ ልብ ውስጥ፡፡
ጉይላዩም ዱ ባርታስ
(ፈረንሳዊ ገጣሚ)
እኔና እናትሽ ተጋብተን ቢሆን ኖሮ ለረዥም ጊዜ በደስታ የምንኖር ይመስልሻል?
ጆን ጌይ
(እንግሊዛዊ ገጣሚና ፀሐፊ ተውኔት) The Dagger’s opera
በፍቅር ላይ ዲሞክራሲ ሲተገበር ዝሙት ይባላል፡፡
ኤች.ኤል.ሜንከን
(አሜሪካዊ ጋዜጠኛ፣ ሃያሲና አርታኢ)
ሚስቶች፤ ለጐረምሳ ወንዶች ውሽሞች፣ በመካከለኛ እድሜ ላሉት ጓደኞች፣ ለሽማግሌዎች ሞግዚቶች ናቸው፡፡
ፍራንሲስ ቤከን
(እንግሊዛዊ ፈላስፋ፣ ከፍተኛ ባለስልጣንና ጠበቃ)
ብዙ ሴቶችን በመጐምዠት አይቼአለሁ፡፡ በልቤ ብዙ ጊዜ ዝሙት ፈፅሜአለሁ፡፡ እግዚአብሔር ለዚህ ይቅር ይለኛል፡፡
ጂሚ ካርተር
(የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩ ለplayboy በሰጡት ቃለምልልስ)
ካገቡ ወንዶች ጋር አንሶላ አልጋፈፍም ስል በትዳራቸው ደስተኛ ሆነው ከሚኖሩ ወንዶች ጋር አልተኛም ማለቴ ነው፡፡
ብሪት ኡክላንድ
(ስዊድናዊ የፊልም ተዋናይ)