Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 14 January 2012 10:27

የፖለቲካ ጥግ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አባቴ ሁልጊዜ በየሰርጉ ላይ ሙሽራ፣ በየቀብሩ ላይ አስከሬን መሆን ይፈልግ ነበር፡፡

ኒኮላስ ሩዝቬልት

(አሜሪካዊ ጋዜጠኛ ቴዎዶር ሩስቬልትን አስመልክቶ የተናገረው)

ፖለቲካ በጣም ትልቅ ጉዳይ በመሆኑ እንደዘበት ለፖለቲከኞች የሚተው አይደለም የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሻለሁ፡፡

ቻርለስ ደ ጐል

(የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት የነበሩ)

 

 

ሰዎች ለማሰብ ጊዜ፣ ጥረትና ዝግጅት እንደሚያስፈልግ የተገነዘቡ አይመስልም፡፡ ፖለቲከኞች ንግግር በማድረግ ከመጠን በላይ ከመጠመዳቸው የተነሳ ለማሰብ ጊዜ የላቸውም፡

በትራንድ ረስል

(እንግሊዛዊ ፈላስፋና የሂሳብ ሊቅ)

ፖለቲከኞች ከዋሻው መጨረሻ ብርሃን ሲመለከቱ ተጨማሪ ዋሻ እንዲሰራ የሚያዙ ሰዎች ናቸው፡፡

ሰር ጆን ኪዊንተን

(እንግሊዛዊ የባንክ ባለሙያ)

ፖለቲከኞች የትም ቢሆን አንድ ናቸው፡፡ ወንዝ በሌለበትም ስፍራ ድልድይ ለመስራት ቃል ይገባሉ፡፡

ኒኪታ ክሩስቼቭ

(የሶቭየት ከፍተኛ ባለስልጣን)

እውቅና ሊሰጠኝ ያልፈቀደ እሱ ተቃውሞኛል፡፡

ፍራንትዝ ፋኖን

(የማርቲንኩዋን ማህበራዊ ሳይንቲስት፣ ፊዚሺያንና የሥነ አዕምሮ ባለሙያ)

የሚቃወሙኝን አከብራቸዋለሁ፤ ነገር ግን ልታገሳቸው አልችልም፡፡

ቻርለስ ደጐል

(የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት የነበሩ 1890-1970)

ፖለቲከኛ ወላጅ አልባ ሆኖ መወለድና ላጤ ሆኖ መቅረት አለበት፡፡

ሌዲ በርድ ጆንሰን

(የአሜሪካ ቀዳሚ እመቤት)

ፖለቲከኛ፤ ስራውን ላለማጣት ሲል ማናቸውንም ነገሮች ከማድረግ ወደኋላ አይልም - አርበኝነትን ጨምሮ፡፡

ዊሊያም ራንዶልፍ ኸርስት

(የአሜሪካ ጋዜጣ አሳታሚ የነበረ)

ፖለቲከኛ የመንግስት አውቶሞቢል መጠባበቂያ (ትርፍ) ጐማ ነው፡፡

ጆን ናንሴ ጋርነር

(የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበረ 1868-1967)

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ቢሆኑም እንኳ አንዳንዴ እርቃናቸውን መቆም አለባቸው፡፡

ቦብ ዳይላን

(አሜሪካዊ ዘፋኝ)

 

 

Read 3457 times Last modified on Saturday, 14 January 2012 10:30