የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ከግብፁ ኦርቶዶክስ ኮፒቲክ ቤተክርስቲያን ጳጳስ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 2ኛ በተደረገላቸው ጥሪ መሠረት ዛሬ ግብፅ ይገባሉ፡፡
ፓትሪያሪኩ ስምንት አባላት ያሉትን የልዑካን ቡድን በመያዝ የአምስት ቀናት ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሏል፡፡
ፓትሪያሪኩ በግብፅ ቆይታቸው በአባይ ጉዳይ ላይ ከግብፁ ኮፕቲክ ቤ/ክርስቲያን ጳጳስ ጋር ውይይት እንደሚያደርጉም ታውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ ገዳማትንና ቤተክርስቲያናትን ይጐበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡