Print this page
Saturday, 22 November 2014 12:24

ለ800 ወጣቶች የትምህርት ድጋፍ ሊደረግ ነው

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ያላቸውንና በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ 600 ሴቶችንና 200 ወንዶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነፃ የትምህርት ዕድል ለመስጠት መዘጋጀቱን የአፍሪካ ሴቶች የትምህርት ፎረም (FAWE) አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና በመጪው ታህሳስ ወር በይፋ በሚጀመረው የትምህርት ድጋፍ፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች የሚገኙና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ሆነው በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡ በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ባህር ዳርና አዋሳ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ 8 ትምህርት ቤቶች፣ ከዘጠነኛ እስከ 12ኛ ክፍል ባሉ ተማሪዎች ላይ ተግባራዊ የሚደረገው ይኸው የስኮላርሽፕ ድጋፍ፣ ተማሪዎቹ የዓለም አቀፍ ነፃ የትምህርት ዕድል እስከመስጠት ድረስ የሚዘልቅ መሆኑም ታውቋል፡፡

Read 1399 times