Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Friday, 06 January 2012 08:28

በለንደን ኦሎምፒክ ለኢትዮጵያ 12 ሜዳልያዎች ታቀዱ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በለንደን በሚደረገው 30ኛው ኦሎምፒያድ ላይ ኢትዮጵያ በሚኖራት ተሳትፎ የሚመዘገበውን ውጤት ከአራት አመት በፊት ቤጂንግ ከተገኘው  በ40 በመቶ የማሳደግ ዓላማ  እንዳለው ገለፀ፡፡ አጠቃላይ ዝግጅቱን ከ1 ዓመሩን ያስታወቀው ኮሚቴው በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን 60 አሰልጣኞችና ሌሎች ባለሙያዎች እንዲሁም በለንደን ኦሎምፒክ ተሳትፎ ይደረግባቸዋል በተባሉት የአትሌቲክስ፤ የዋና፤ የቦክስና የተክዋንዶ ስፖርቶች የታቀፉ 120 ስፖርተኞች ልምምድ መጀመራቸውንም አረጋግጧል፡፡

በአትሌቲክስ ከሚያዙ አትሌቶች ስምንቱ በውጭ አገር ለመሰልጠን የሚያስችላቸውን ስኮላርሺፕ አግኝተው ሙሉ ወጭያቸውን በመሸፈን ዝግጅት እንዲጀምሩ መደረጉንም አመልክቷል፡፡በአገር አቀፍ ደረጃ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ከ3 ሳምንት በፊት ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አገራችን በለንደን ኦሎምፒክ በሚኖራት ተሳትፎ ላይ ከወዲሁ ትኩረት በማድረግ ምነቀሳቀሱ ተገቢ ነው፡፡ የኦሎምፒክ ኮሚቴው በዕቅዱ በለንደን ኦሎምፒክ 12 ሜዳልያዎችን 4 ወርቅ፤4 ብርና 4 ነሐስ ሜዳልያዎችን ለማግኘት ይፈልጋል፡፡ ይንንም በተሳካ ዝግጅት ለመተግበር 30 ሚሊዮን ብር ለበጀት እንደሚያስፈልገውም አሳውቋል፡የኬንያ ኦሎምፒክ  ባንፃሩ በእንግሊዝ በተዘጋጀለት የስፖርት ማዕከል ጋር በመንቀሳቀስ የተለየ ትኩረት ይዞ እየሰራ ነው፡፡ ከ1 ዓመት በፊት በእንግሊዟ ከተማ ብሪስቶል በሚገኘው የፍሊንተን ኮሌጅ በ1.3 ሚሊዮን ፓውንድ የተሰራው የስፖርት ኮምፕሌክስን የቀድሞው የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤትና አሁን የኬንያን ኦሎምፒክ ኮሚቴን በሊቀመንበርነት የሚመራው ኪፕቾጌ ኬኖ መርቆ መክፈቱ ይታወሳል፡፡ በብሪስቶል አካዳሚ ስፖርት ኮምፕሌክስ ቅጥር ግቢ የሚገኘው ይህ ማእከል በ1968 እና በ1972 እኤአ ሁለት የወርቅ ሜዳልያ ለኬንያ ባስገኘው ታዋቂ ሯጭ ኪፕ ኬኖ ተሰይሟል፡፡ አሁን 70ኛ ዓመቱን የያዘው ኪፕ ኬኖ በ1500 በ1968ቱ የሜክሲኮ ኦሎምፒክ እንዲሁም ከ4 ዓመታት በሃላ በሙኒክ ኦሎምፒክ በ3ሺ መሰናክል ሁለት የወርቅ ሜዳልያዎችን በማስመዝገብ ለአፍሪካ ፈርቀዳጅ ታሪኮችን የሰራ ነው፡፡ የብሪስቶሉ ኪፕ ኬኖ የስፖርት ኮምፕሌክስ የኬንያ ኦሎምፒክ ቡድን ለ30ኛው የለንደን ኦሎምፒያድ የዝግጅትና የማረፍያ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፡፡ለንደን በፊት በኦሎምፒክ የውድድር መድረክ ለ11 ጊዜ የተሳተፈችው ኢትዮጵያ በድምሩ 38 ሜዳልያዎች 18 ወርቅ፤ 6 ብርና14 ነሐስ አግኝታለች፡፡  ከ4 ዓመት በቤጂንግ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ በ7 ሜዳልያዎች 4 ወርቅ ፤ 1ብርና 2 ነሐስ  በመውሰድ 5ኛ ነበረች፡፡ኬንያ በበኩሏ በ12 ጊዜ ተሳትፎዋ 75 ሜዳልያዎች 22 ወርቅ፤ 28 ብርና 24 ነሐስ አስመዝግባለች፡፡ ከ4 ዓመታት በፊት ቤጂንግ አስተናግዳው በነበረው 29ኛው ኦሎምፒያድ ኬንያ በአትሌቲክስ ውድድሮች 14 ሜዳልያዎችን 6 ወርቅ ፤ 4ብርና 4 ነሐስ ሰብስባ ከተሳታፊ አገራት 3ኛ ደረጃ ማግኘቷ የሚታወስ ነው፡፡ በሌላ በኩል 205 አገራትን የወከሉ 10ሺ 500 አትሌቶች የሚሳተፉበትና 7 ወራት የቀሩት 30ኛው የለንደን ኦሎምፒያድ ከፍተኛ የፀጥታና ደህንነት እንዲኖረው በመታቀዱ ወጪው እየናረ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡ በአጠቃላይ መሰናዶው 20 ቢሊዮን ፓውንድ ይወጣበታል ተብሎ የሚጠበቀው የ2012 የለንደን ኦሎምፒክ በተጠናከረ ፀጥታ እና የደህንነት ጥበቃ ለማካሄድ ብቻ ሰሞኑን ይፋ በሆነው አዲስ እቅድ ጋር በተያያዘ ክስ ከ9.3 ቢሊዮን ፓውንድ ይጠይቃል፡፡  በ2005 እኤአ ላይ ለፀጥታና ደህንነት ጥበቃ ወጪ ይደረጋል ተብሎ የተገመተው እስከ 2.4 ቢሊዮን ፓውንድ ነበር፡፡  ሰሞኑን የወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት የእንግሊዝ መንግስት ለኦሎምፒኩ ፀጥታ እና ደህንንት ሲባል እና ይህንኑ በመተግበር ከፍተኛ ሚና ለሚኖራቸው የፀጥታ ሃይሎች በአጠቃላይ 271ሚሊዮን ፓውንድ በክፍያ ወጪ 30ኛውን ኦሎምፒያድ በተሟላ የፀጥታና ደህንንት ጥበቃ ለማካሄድ አስቀድሞ 10ሺ የፀጥታ ሃይሎች ብቻ እንደሚያስፈልጉ ተገምቶ የነበረ ቢሆንም ይህ ቁጥር ወደ 23 700 አድጓል፡፡  ለለንደን ኦሎምፒክ  እስከዛሬ 6.6 ሚሊዮን ትኬቶች ተሸጠው 527 ሚሊዮን ፓውንድ ገቢ መደረጉን አዘጋጅ ኮሚቴው የገለፀ ሲሆን የእንግሊዝ መንግስት በለገሰው ድጋፍ 700ሺ ፓውንድ በትኬት ግዢ ለተጋባዥ እንግዶች እና ሌሎች ታዳሚዎች ወጪ መደረጉም ታውቋል፡፡በተያያዘ ቢቢሲ በሰራው ጥናት በኦሎፒክ ተሳታፊ አገራት ከሆኑት በታዳጊና በመካከለኛ ገቢ የሉ ህዝቦት ከ21 ሰዎት 18 ያህሉ በሚኖረው ስኬታማነት ብሔራዊ ኩራት እንደሚሰጣቸው አረጋገጠ፡፡ ቢቢሲ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሰባሰበው በዚህ ድምጽ አጠቃላይ ግምገማ መሠረት በኦሎምፒክ መድረክ የሚገኙ ውጤቶችና ታሪካዊ ክብረወሰኖች በተለይ በታዳጊና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ከፍተኛ ዕመርታ ያለውን መነቃቃት ይፈጥራል፡፡ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የኦሎምፒክ ህልም ዛሬም ቢሆን ህዝቦችን ማነቃቃቱን እንደኮራበት የገለፁ ሲሆን አጋሮቻቸውን በመወከል በታላቁ የስፖርት መድረክ በከፍተኛ ብቃት የሚሳተፉ አትሌቶችን አድንቆ የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የዓለም አገራትን በማስተባበር የሚጫወቱት ሚና ምስጋና ይግባው ብሏል፡፡ ቢቢሲ ጥናቱን የሰራው በዓለም ዙሪያ 21,061 ሰዎች የሰጡትን ድምጽ መሠረት አድርጐ ሲሆን 91 ኬንያውያን፣ 86 ፍሊፕናዊያን፣ 84 ቱርካውያንና 83 ኢንዶኔዣውያን አገሮቻቸው በኦሎምፒክ ሚኆግራቸው ተሳትፎና ውጤታማነት ኩራት ይሰማናል የሚል አስተያየት መስጠታቸውን አብራርቷል፡፡ ባደጉት አገራት ይሄው ስሜት ከ50-60% ብቻ የሚለካ መሆኑንም አረጋግጧል፡፡

 

 

 

 

Read 3339 times Last modified on Friday, 06 January 2012 08:33