በዓለም የስፖርት እንቅስቃሴ ዘንድሮ የተገኘው አጠቃላይ ገቢ 118.7 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ከባለፈው አመት በ2 % ወርዷል፡፡ ከቲኬት ሽያጭ 39 ቢሊዮን ዶላር፤ ከሚዲያ መብት 26.9 ቢሊዮን፤ ከስፖንሰርሺፕ 35.1 ቢሊዮን እና ከተለያዩ ንግድ እንቅስቅሴዎች 17.5 ቢሊዮን ዶላር በዓለም ዙርያ ገቢ መደረጉን የገለፀው ፕራይስዎተርሃውስ ኩፐርስ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ገቢው በ10% እድገት እንደሚያሳይ አስታውቋል፡፡ከ2006 ጀምሮ በነበሩት አራት የውድድር ዘመናት ብራዚል ቻይና ሩስያና ህንድ በስፖርቱ ወጪ የሚያደርጉት ገንዘብ በ7.7% ማሳደጋቸውን የገለፀው ሪፖርቱ የሰሜን አሜሪካ አህጉር ከአጠቃላይ ገቢው 41% ድርሻ በመያዝ 49.9 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዳስመዘገበና አውሮፓ ፤ መካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ በጋራ 42.8 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተከታታይ ደረጃ እንደወሰዱ አረጋግጧል፡፡