Saturday, 23 August 2014 11:10

ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ የግል ትምህርት ተቋማት ጉባኤን ያዘጋጃል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

              ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ 12ኛውን በአፍሪካ በግሉ ዘርፍ በሚገኙ የትምህርት ተቋማት ላይ የሚያተኩረውን አህጉራዊ ጉባኤ በዛሬው እለት ያስተናግዳል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ጉባኤውን አስመልክቶ እንዳስታወቀው፤ ይህን መሰሉ ጉባኤ ላለፉት 11 ዓመታት በየዓመቱ አፍሪካውያን ተመራማሪዎችን በአንድ መድረክ እያገናኘ እርስ በእርስ እንዲማማሩና የወደፊቷን አፍሪካ የተሻለች ለማድረግ እንዲቻል እየተደረገ ያለውን ጥረት በማገዝ የመሪነቱን ሚና በመጫወት ላይ ይገናኛል ብሏል፡፡ በዘንድሮው ዓመት የሚካሄደው 12ኛው አህጉር አቀፍ ጉባኤም “Retrospect and Prospect of Private Higher Education in Africa” በሚል ጭብጥ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) የስብሰባ አዳራሽ በዛሬው እለት እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡ በየዓመቱ የሚካሄደው ጉባኤው፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ የተለያዩ አገሮች ከሚገኙ የትምህርትና የምርምር ተቋማት የተውጣጡ ታዋቂና የተመረጡ ምሁራን የሚሳተፉበት የምርምርና የውይይት መድረክ ነው ተብሏል፡፡

Read 1733 times