Saturday, 09 August 2014 11:15

የመካከለኛው ምስራቅ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ከ21 ቢ. ብር በላይ ያንቀሳቅሳሉ

Written by 
Rate this item
(5 votes)

የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ኩባንዎች በኢትዮጵያ ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያንቀሳቅሱ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች እንዳላቸው  ወርልድ ቡሊቲን ዘገበ፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ያወጣውን መረጃ በመጥቀስ ዘገባው እንዳለው፣ ኩባንያዎቹ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች 179 ያህል የምርት፣ የግብርና፣ የሪል እስቴትና የማሽነሪ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን እያንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ 80 የሚደርሱ ፕሮጀክቶች የአገሪቱ መንግስት ትኩረት በሰጠው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ውስጥ እንደሚገኙ ሲታወቅ 35 ያህሉ ደግሞ ለዘርፉ ግብዓት በሚያመነጨው የግብርናው ዘርፍ እንደተካተቱ ዘገባው አመልክቷል፡፡
በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ከተሰማሩት የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ቀዳሚውን ስፍራ የምትይዘው ሳኡዲ አረቢያ ስትሆን  አገሪቱ በኢትዮጵያ 86 ፕሮጀክቶችን እያከናወነች እንደምትገኝ ዘገባው ጠቁሞ፤ ከመካከለኛው ምስራቅ አገራት በተጨማሪ ሱዳን፣ ግብጽ፣ ደቡብ አፍሪካና ናይጀሪያን የመሳሰሉ የአፍሪካ አገራትም በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ አመልክቷል፡፡

Read 2077 times