- በእኔ አስተያየት ሥልጣን በማንም እጅ ላይ ቢሆን መታመን የለበትም፡፡
ዊሊያም ጆንስ
(እንግሊዛዊ ዳኛና ኦሬንታሊስት)
- ህዝብ ሥልጣን አለኝ ብሎ ሲያስብ ሥልጣን አለው፡፡
ዊሊያም ዊች ፎውለር -
(አሜሪካዊ ፖለቲከኛ)
- ሥልጣን ውሽማዬ ናት፡፡ ሌሎች እንዳይቀሙኝ ወይም እንዳያማልሉብኝ ጠንክሬ ሰርቻለሁ፡፡
ናፖሊዮን (አንደኛ)
(የፈረንሳይ ንጉሰ ነገስት)
- በአንድ ሰው በጐ ፈቃድ ህይወትን መምራት፣ የሰው ልጆች ሁሉ የመከራ ሰበብ ሆኗል፡፡
ሪቻርድ ሁከር
(እንግሊዛዊ የሥነ መለኮት ሊቅ)
- ገደብ የለሽ ሥልጣን የሥልጣኑን ባለቤቶች አዕምሮ ያበላሻል፡፡
ዊሊያም ፒት ዘ ኤልደር
(የእንግሊዝ ጠ/ሚኒስትር - 1708-1778
- ፖለቲከኞች ጌታ ለመሆን ሲሉ አገልጋይ መስለው ይቀርባሉ፡፡
ቻርለስ ደ ጐል
(የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት 1890-1970)
- ጠብመንጃ ጉልበተኛ ያደርገናል፤ ቅቤ ግን ከማወፈር በቀር ፋይዳ የለውም፡፡
ኸርማን ጐንግ
(የጀርመን ናዚ መሪ)
- ሥልጣን ላይ ያለ ጓደኛ ያጣኸው ያህል ነው፡፡
ሔነሪ አዳምስ
(አሜሪካዊ የታሪክ ምሁር)