Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 December 2011 07:55

“የቤተሰብ እቅድ ...15% ወደ 29% አድጎአል”

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ባለፈው እትም ዘላቂ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎትን በሚመለከት የወንዶች ተሳትፎ ምን ይመስላል በሚል ለንባብ ያልነውን መሰረት በማድረግ ላንቺና ላንተ በሚለው ድህረገጽ የተወሰኑ ጥያቄዎች ደርሰውናል፡፡ ጥያቄዎቹን ተባባሪ አዘጋጅዋ አዲስ አለም ብርሀኔ ለባለሙያ በማቅረብ እና በተለያዩ የጥናት ወረቀቶች በመታገዝ ለመላው አንባቢ ይድረስ ብላለች፡፡

ጥያቄ፤ ቫዜክቶሚ ማለት ምን ማለት ነው?
መልስ፤ ቫዜክቶሚ ማለት የወንድ የዘር ፍሬ  ወደሴቷ ማህጸን እንዲያልፍ የሚያደርገውን አነስተኛ ቲዩብ መስመሩን በመቁረጥ የሚሰራ በጣም አነስተኛ ቀዶ ሕክምና ነው፡፡ ቫዜክቶሚ ልጅ መውለድ ለማይፈልጉ ወንዶች ለዘለቄታው የሚሰጥ የህክምና ዘዴ ነው፡፡
ጥ - ቫዜክቶሚ ቀዶ ሕክምናው ሲሰራ ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል?
መ - ቫዜክቶሚ ሲሰራ በቀጥታ ቀዶ ሕምናው ላይ የሚጠፋው ሰአት ከ15 ደቂቃ የበለጠ ጊዜ አይወስድም ፡፡ ምናልባትም ከኦፕራሲዮኑ ጋር በተያያዘ ሌሎች አስተዳደራዊ ስራዎች ስለሚኖሩ በጥቅሉ አንድ ሰአት ሊወስድ ይችላል፡፡ ነገር ግን በቀጥታ ከህክምናው ስራ ጋር በተያያዘ የሚወስደው ጊዜ ከአስራ አምስት ደቂቃ የማይበልጥ ነው፡፡
ጥ - ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ ሰውየው ምን ያህል ጊዜ አልጋ ይይዛል?
መ - ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ አልጋ ላይ መቆየት አይኖርም፡፡ ከተወሰነ ሰአት ቆይታ በሁዋላ ኦፕራሲዮኑ የተሰራላቸው ሰዎች ከጤና ተቋሙ ወደቤታቸው እንዲሄዱ ይደረጋል፡፡ ከዚያም በሁዋላ ምንም ሳይቆዩ ወደተለመደው ስራቸው መግባት ይችላሉ፡፡
ጥ - ቫዜክቶሚ ቤተሰብን ለዘለቄው ለማቀድ ምን ያህል ትክክለኛው መንገድ ነው?
መ - ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ የወንዱ ስፐርም ወደሴቷ ማህጸን ስለማይፈስ ልጅ ማስረገዝ አይችልም፡፡ ስለዚህ አስተማማኝ የዘለቄታ ወሊድ መከላከያ ዘዴ ነው፡፡
ጥ - ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ ወዲያውኑ ውጤታማ ይሆናልን ?
መ - ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ እለቱን ወይንም ከሰሞኑ ግንኙነት ቢደረግ ልጅ አይረገዝም ማለት አይቻልም፡፡ቀዶ ሕክምናው ከመደረጉ በፊት የነበረው ስፐርም በፈሳሽ ውስጥ ሊኖር ስለሚችል የግብረስጋ ግንኙነት ቢደረግ መከላከያ ኮንዶም መጠቀም ይመረጣል፡፡ ስለዚህ ቢያንስ ከ 15-20 ጊዜ የወሲብ ግንኙነት ካደረጉ በሁዋላ ከሐኪም ጋር በመመካከር ቀጣዩን ሕይወት መምራት ይቻላል፡፡
ጥ - ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ የሚመረተው ስፐርም ምን ይሆናል?
መ - ይህ ተፈጥሮአዊ የሆነ ነገር ነው፡፡ ቫዜክቶሚ ተሰራም አልተሰራም የሚኖር ጤነኛና ተፈጥሮአዊ የሆነ አካሄድ አለው፡፡  የተመረተው ስፐርም ከጥቅም ላይ ካልዋለ ሰውነት መልሶ ይጠቀምበታል፡፡ ቫዜክቶሚ በመሰራቱም ስፐርም መመረቱን አያቋርጥም፡፡ ነገር ግን በሰውነት ውስጥ ስለሚቀር ሰውነት እንደገና ይጠቀምበታል፡፡
ጥ - ቫዜክቶሚ የተሰራለት ወንድ እንደቀድሞው የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ ይችላልን ?
መ - ለዚህ የሚሆነውን መልስ የሚሰጡን ቀደም ሲል ቫዜክቶሚ የተሰራላቸው አንድ ወንድ ናቸው፡፡
“አሁንማ ልጅ ቢወለድ በምን አሳድጋለሁ የሚል ስጋት ስለሌለብኝ እንደልቤ ከሚስ ጋር መደሰት ጀምሬአለሁ፡፡ ነጻነቱ በጣም ደስ ይላል፡፡ ስምንተኛው ልጅ ሲወለድ የነበረብኝ ሀዘን ቀላል አልነበረም፡፡ ምክንያቱም ኑሮው አንገዳገደኝ፡፡አሁን ግን ይሄ ኦፕራሲዮን ከተሰራልኝ በሁዋላ እኔም ሚስም ሰቀቀን የሚባል ነገር አክትሞልናል፡፡ በእድሜም ገና ልጆች ስለሆንን እየተደሰትን እንኖራለን፡፡ ኦፕራሲዮን በመደረጌ ምንም የቀረብኝ ወይንም የቀነሰብኝ ነገር የለም፡፡”
ከላይ አስተያየታቸውን እንደሰጡት ሰው ቫዜክቶሚ መሰራቱ የወሲብ ፍላጎትን ወይንም ድርጊትን በምንም መልኩ የማያውክ መሆኑ የተረጋገጠ ነው፡፡ ቫዜክቶሚ ስፐርም ወደ ሴቷ ማህጸን እንዳይገባ ከማገድ በስተቀር የተቀረውን ተፈጥሮአዊ ሁኔታ በፍጹም አይነካም፡፡
ጥ - ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ እንደገና ወደቀድሞው ሁኔታ የሚመልስ ሕክምና ይኖራልን ?
መ - ቫዜክቶሚ ከመሰራቱ በፊት አንድ ወንድ ከዚህ በሁዋላ ልጅ መውለድ አልፈልግም ብሎ በበቂ ሁኔታ አስቦበት መወሰን ይጠበቅበታል፡፡ የዚህም ምክንያቱ ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ እንደገና ልጅ መውለድ ወደሚችልበት ተፈጥሮአዊ ሁኔታ መመለስ ስለማይቻል ነው፡፡
ባጠቃላይም ቫዜክቶሚን በተመለከተ፡-
ምናልባት ግር የሚያሰኙ ነገሮች ቢገጥሙ ጠይቆ መረዳትን ልምድ ማድረግ ይጠቅማል፡፡
ሁልግዜ በቅርብ ከሚገኝና ከሚመርጡት የህክምና ባለሙያ ጋር ውይይት ማድረግን መልመድ ጥሩ መፍትሔ ያስገኛል፡፡
ቫዜክቶሚ ቀላል ፣ደህንነቱ የተጠበቀና ውጤታማ የሆነ የህክምና አገልግሎት ነው፡፡
ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ ማስረገዝ አለማስረገዝ የሚለውን ውጤቱን ለማወቅ የተወሰኑ ሳምንታት መታገስ ያስፈልጋል፡፡
ቫዜክቶሚ ወሲብ መፈጸምን አያውክም፡፡
ቫዜክቶሚ ቋሚ የወሊድ መከላከያ ዘዴ ሲሆን ምናልባት ልጅ እፈልጋለሁ በሚል ወደቀድሞው ተፈጥሮአዊ ሁኔታ መመለስ ግን አይቻልም፡፡
***
በእንግሊዝኛው ቃል VASECTOMI  የተሰኘው ወንዶች ለዘላቂ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት የሚጠቀሙበት የህክምና ዘዴ ለብዙዎች ጥርጣሬን የሚያጭርና የተሳሳቱ ሀሳቦችን በማመንጨት ለድርጊቱ ፈቃደኝነት እንዳያሳዩ የሚያደርጋቸው መሆኑ እሙን ነው ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ወንዶች የህክምና ዘዴውን ተግባራዊ በማድረግ ያለምንም ችግር ኑሮአቸውን በመምራት ላይ መሆናቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የወንዶቹ ተሳትፎ በተለይም በአገራችን ገና ብዙ ስራን የሚጠይቅ መሆኑን የገለጹት የኢንጀንደር ሔልዝ ኢትዮጵያ አብሪ (access for better  reproductive health ) በአማርኛው የወጣቶችን እንዲሁም የእናቶችን ጤና በማሻሻል ብሩህ ሕይወትን እንዲያገኙ ጥረት ማድረግን የሚመለከተው ፕሮጀክት ዴፕዩቲ ዳይሬክተር አቶ ጀማል ካሳው ናቸው፡፡
እንደ አቶ ጀማል ማብራሪያ የእርግዝና መከላከያዎች የተለያዩ የራሳቸው ባህሪያት ያላቸው ሲሆን በመጠኑ እስኪለመዱ ድረስ በሰውነት ላይ አንዳንድ ለውጦችን ሊያመጡ የሚችሉ ሲሆን ከታገሱት ግን ወደትክክለኛው ሁኔታ ለመመለስ ጊዜ አይፈጅም ፡፡ነገር ግን ወንዶቹ የቤተሰብ እቅድ እንዲኖር ቢፈልጉም ከሚስ ቶቻቸው ጋር አብረው ወደ ጤና ተቋሙ ስለማይሄዱና የሚወሰዱትን መከላከያዎች ባህሪይ ምን እንደሆነ ስለማይረዱ በሴቶቹ ላይ ተጽእኖ ያደርጋሉ፡፡ የቤተሰብ እቅድ እናድርግ በሚለው ቢስማሙም የሚከተለውን ጊዜያዊና አነስተኛ የሆነ የባህርይ ወይንም  የጤና መዛባቱን አልቀበልም በሚለው ተጽእኖ መከላከያው እንዲቋረጥ ስለሚያደርጉ በዚህ መሀል ልጅ የመውለድ አጋጣሚው ይከሰታል፡፡ ይህ እንግዲህ ያልተፈለገ እና ያልታቀደ ስለሚሆን ችግር ማስከተሉ አይቀርም ፡፡ በዚህ ረገድ ብዙ ወንዶች ሴቶቹ ለሚወስዱት የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተባባሪ ናቸው ለማለት አያስደፍርም፡፡
ከአስራ አምስት አመት ወዲህ ያለው የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚነት በየአምስት አመቱ በእጥፍ እያደገ የመጣበት ሁኔታ ይታያል ፡፡ ባለፈው አመት በተደረገው ጥናት የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚነት ከ15 ወደ 29 አድጎአል፡፡ የዚህ ተጠቃሚዎች በአብዛኛው ሴቶቹ ናቸው፡፡ የወንዶቹ የቤተሰብ እቅድ ዘዴዎች ግን ከ0.1 በታች ነው፡፡ እነርሱም እንደኮንዶምና ቋሚ የወሊድ መከላከያ ቫዜክቶሚ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ በእርግጥ የወንዶቹ ተጠቃሚነት ወይንም እራሳቸው የሚያደርጉት ተሳትፎ የሚጠበቀውን ያህልም ባይሆን የተወሰነ ተሳትፎ እንዳላቸው የሚያሳየው ከሚስቶቻቸው ጋር ተመካክረው ሴቶቹ መከላከያውን እንዲወስዱ መፍቀዳቸው ነው፡፡ ወንዶች መከላከያው እንዳይወሰድ በሚያደርጉበት አካባቢ ሁሉ ሴቶች መከላከያውን ቢወስዱም እንኩዋን የሚጠቀሙት በጣም በችግር መሆኑን ብዙዎች ይመሰክራሉ፡፡ስለዚህ የወንዶቹ ተሳትፎ በአብዛኛው ለባለቤቶቻቸው ተጠቃሚነት ከማማከርና ከመፍቀድ የዘለለ ሆኖ አይታይም እንደ አቶ ጀማል ካሳው፡፡
አቶ ጀማል አክለውም “የወንዶች የቤተሰብ እቅድ ተሳትፎ ምን ይመስላል የሚለውን ስንመለከት በአገራችን በጣም ዝቅተኛ ከሚባል ደረጃ ላይ ያለ ነው፡፡ በእርግጥ በአለም አቀፍ ደረጃም ያለው መረጃ ዝቅተኛ መሆኑን የሚያመላክት ሲሆን ይህም የመነጨው በተለምዶ የተዋልዶ ጤና የሴቶች ጉዳይ ተደርጎ ስለሚታሰብ ነው፡፡ ወንዶች ብዙውን ጊዜ የቤተሰብ እቅድ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ግንዛቤው ስለሌላቸው ምን እንደሚጠበቅባቸው የማያውቁበት ሁኔታ አለ፡፡ ስለዚህ ወንዶቹ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ላይ ያላቸው ተሳትፎ አለ የሚባል አይደለም” ብለዋል፡፡

ጥያቄ፤ ቫዜክቶሚ ማለት ምን ማለት ነው?

መልስ፤ ቫዜክቶሚ ማለት የወንድ የዘር ፍሬ  ወደሴቷ ማህጸን እንዲያልፍ የሚያደርገውን አነስተኛ ቲዩብ መስመሩን በመቁረጥ የሚሰራ በጣም አነስተኛ ቀዶ ሕክምና ነው፡፡ ቫዜክቶሚ ልጅ መውለድ ለማይፈልጉ ወንዶች ለዘለቄታው የሚሰጥ የህክምና ዘዴ ነው፡፡

- ቫዜክቶሚ ቀዶ ሕክምናው ሲሰራ ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል?

- ቫዜክቶሚ ሲሰራ በቀጥታ ቀዶ ሕምናው ላይ የሚጠፋው ሰአት ከ15 ደቂቃ የበለጠ ጊዜ አይወስድም ፡፡ ምናልባትም ከኦፕራሲዮኑ ጋር በተያያዘ ሌሎች አስተዳደራዊ ስራዎች ስለሚኖሩ በጥቅሉ አንድ ሰአት ሊወስድ ይችላል፡፡ ነገር ግን በቀጥታ ከህክምናው ስራ ጋር በተያያዘ የሚወስደው ጊዜ ከአስራ አምስት ደቂቃ የማይበልጥ ነው፡፡

- ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ ሰውየው ምን ያህል ጊዜ አልጋ ይይዛል?

- ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ አልጋ ላይ መቆየት አይኖርም፡፡ ከተወሰነ ሰአት ቆይታ በሁዋላ ኦፕራሲዮኑ የተሰራላቸው ሰዎች ከጤና ተቋሙ ወደቤታቸው እንዲሄዱ ይደረጋል፡፡ ከዚያም በሁዋላ ምንም ሳይቆዩ ወደተለመደው ስራቸው መግባት ይችላሉ፡፡

- ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ የወንዱ ስፐርም ወደሴቷ ማህጸን ስለማይፈስ ልጅ ማስረገዝ አይችልም፡፡ ስለዚህ አስተማማኝ የዘለቄታ ወሊድ መከላከያ ዘዴ ነው፡፡

- ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ ወዲያውኑ ውጤታማ ይሆናልን ?

- ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ እለቱን ወይንም ከሰሞኑ ግንኙነት ቢደረግ ልጅ አይረገዝም ማለት አይቻልም፡፡ቀዶ ሕክምናው ከመደረጉ በፊት የነበረው ስፐርም በፈሳሽ ውስጥ ሊኖር ስለሚችል የግብረስጋ ግንኙነት ቢደረግ መከላከያ ኮንዶም መጠቀም ይመረጣል፡፡ ስለዚህ ቢያንስ ከ 15-20 ጊዜ የወሲብ ግንኙነት ካደረጉ በሁዋላ ከሐኪም ጋር በመመካከር ቀጣዩን ሕይወት መምራት ይቻላል፡፡

- ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ የሚመረተው ስፐርም ምን ይሆናል?

- ይህ ተፈጥሮአዊ የሆነ ነገር ነው፡፡ ቫዜክቶሚ ተሰራም አልተሰራም የሚኖር ጤነኛና ተፈጥሮአዊ የሆነ አካሄድ አለው፡፡  የተመረተው ስፐርም ከጥቅም ላይ ካልዋለ ሰውነት መልሶ ይጠቀምበታል፡፡ ቫዜክቶሚ በመሰራቱም ስፐርም መመረቱን አያቋርጥም፡፡ ነገር ግን በሰውነት ውስጥ ስለሚቀር ሰውነት እንደገና ይጠቀምበታል፡፡

- ቫዜክቶሚ የተሰራለት ወንድ እንደቀድሞው የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ ይችላልን ?

- ለዚህ የሚሆነውን መልስ የሚሰጡን ቀደም ሲል ቫዜክቶሚ የተሰራላቸው አንድ ወንድ ናቸው፡፡

“አሁንማ ልጅ ቢወለድ በምን አሳድጋለሁ የሚል ስጋት ስለሌለብኝ እንደልቤ ከሚስ ጋር መደሰት ጀምሬአለሁ፡፡ ነጻነቱ በጣም ደስ ይላል፡፡ ስምንተኛው ልጅ ሲወለድ የነበረብኝ ሀዘን ቀላል አልነበረም፡፡ ምክንያቱም ኑሮው አንገዳገደኝ፡፡አሁን ግን ይሄ ኦፕራሲዮን ከተሰራልኝ በሁዋላ እኔም ሚስም ሰቀቀን የሚባል ነገር አክትሞልናል፡፡ በእድሜም ገና ልጆች ስለሆንን እየተደሰትን እንኖራለን፡፡ ኦፕራሲዮን በመደረጌ ምንም የቀረብኝ ወይንም የቀነሰብኝ ነገር የለም፡፡”

ከላይ አስተያየታቸውን እንደሰጡት ሰው ቫዜክቶሚ መሰራቱ የወሲብ ፍላጎትን ወይንም ድርጊትን በምንም መልኩ የማያውክ መሆኑ የተረጋገጠ ነው፡፡ ቫዜክቶሚ ስፐርም ወደ ሴቷ ማህጸን እንዳይገባ ከማገድ በስተቀር የተቀረውን ተፈጥሮአዊ ሁኔታ በፍጹም አይነካም፡፡

ጥ - ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ እንደገና ወደቀድሞው ሁኔታ የሚመልስ ሕክምና ይኖራልን ?

መ - ቫዜክቶሚ ከመሰራቱ በፊት አንድ ወንድ ከዚህ በሁዋላ ልጅ መውለድ አልፈልግም ብሎ በበቂ ሁኔታ አስቦበት መወሰን ይጠበቅበታል፡፡ የዚህም ምክንያቱ ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ እንደገና ልጅ መውለድ ወደሚችልበት ተፈጥሮአዊ ሁኔታ መመለስ ስለማይቻል ነው፡፡

ባጠቃላይም ቫዜክቶሚን በተመለከተ፡-

ምናልባት ግር የሚያሰኙ ነገሮች ቢገጥሙ ጠይቆ መረዳትን ልምድ ማድረግ ይጠቅማል፡፡

ሁልግዜ በቅርብ ከሚገኝና ከሚመርጡት የህክምና ባለሙያ ጋር ውይይት ማድረግን መልመድ ጥሩ መፍትሔ ያስገኛል፡፡

ቫዜክቶሚ ቀላል ፣ደህንነቱ የተጠበቀና ውጤታማ የሆነ የህክምና አገልግሎት ነው፡፡

ቫዜክቶሚ ከተሰራ በሁዋላ ማስረገዝ አለማስረገዝ የሚለውን ውጤቱን ለማወቅ የተወሰኑ ሳምንታት መታገስ ያስፈልጋል፡፡

ቫዜክቶሚ ወሲብ መፈጸምን አያውክም፡፡

ቫዜክቶሚ ቋሚ የወሊድ መከላከያ ዘዴ ሲሆን ምናልባት ልጅ እፈልጋለሁ በሚል ወደቀድሞው ተፈጥሮአዊ ሁኔታ መመለስ ግን አይቻልም፡፡

***

በእንግሊዝኛው ቃል VASECTOMI  የተሰኘው ወንዶች ለዘላቂ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት የሚጠቀሙበት የህክምና ዘዴ ለብዙዎች ጥርጣሬን የሚያጭርና የተሳሳቱ ሀሳቦችን በማመንጨት ለድርጊቱ ፈቃደኝነት እንዳያሳዩ የሚያደርጋቸው መሆኑ እሙን ነው ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ወንዶች የህክምና ዘዴውን ተግባራዊ በማድረግ ያለምንም ችግር ኑሮአቸውን በመምራት ላይ መሆናቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የወንዶቹ ተሳትፎ በተለይም በአገራችን ገና ብዙ ስራን የሚጠይቅ መሆኑን የገለጹት የኢንጀንደር ሔልዝ ኢትዮጵያ አብሪ (access for better  reproductive health ) በአማርኛው የወጣቶችን እንዲሁም የእናቶችን ጤና በማሻሻል ብሩህ ሕይወትን እንዲያገኙ ጥረት ማድረግን የሚመለከተው ፕሮጀክት ዴፕዩቲ ዳይሬክተር አቶ ጀማል ካሳው ናቸው፡፡

እንደ አቶ ጀማል ማብራሪያ የእርግዝና መከላከያዎች የተለያዩ የራሳቸው ባህሪያት ያላቸው ሲሆን በመጠኑ እስኪለመዱ ድረስ በሰውነት ላይ አንዳንድ ለውጦችን ሊያመጡ የሚችሉ ሲሆን ከታገሱት ግን ወደትክክለኛው ሁኔታ ለመመለስ ጊዜ አይፈጅም ፡፡ነገር ግን ወንዶቹ የቤተሰብ እቅድ እንዲኖር ቢፈልጉም ከሚስ ቶቻቸው ጋር አብረው ወደ ጤና ተቋሙ ስለማይሄዱና የሚወሰዱትን መከላከያዎች ባህሪይ ምን እንደሆነ ስለማይረዱ በሴቶቹ ላይ ተጽእኖ ያደርጋሉ፡፡ የቤተሰብ እቅድ እናድርግ በሚለው ቢስማሙም የሚከተለውን ጊዜያዊና አነስተኛ የሆነ የባህርይ ወይንም  የጤና መዛባቱን አልቀበልም በሚለው ተጽእኖ መከላከያው እንዲቋረጥ ስለሚያደርጉ በዚህ መሀል ልጅ የመውለድ አጋጣሚው ይከሰታል፡፡ ይህ እንግዲህ ያልተፈለገ እና ያልታቀደ ስለሚሆን ችግር ማስከተሉ አይቀርም ፡፡ በዚህ ረገድ ብዙ ወንዶች ሴቶቹ ለሚወስዱት የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተባባሪ ናቸው ለማለት አያስደፍርም፡፡

ከአስራ አምስት አመት ወዲህ ያለው የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚነት በየአምስት አመቱ በእጥፍ እያደገ የመጣበት ሁኔታ ይታያል ፡፡ ባለፈው አመት በተደረገው ጥናት የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚነት ከ15 ወደ 29 አድጎአል፡፡ የዚህ ተጠቃሚዎች በአብዛኛው ሴቶቹ ናቸው፡፡ የወንዶቹ የቤተሰብ እቅድ ዘዴዎች ግን ከ0.1 በታች ነው፡፡ እነርሱም እንደኮንዶምና ቋሚ የወሊድ መከላከያ ቫዜክቶሚ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ በእርግጥ የወንዶቹ ተጠቃሚነት ወይንም እራሳቸው የሚያደርጉት ተሳትፎ የሚጠበቀውን ያህልም ባይሆን የተወሰነ ተሳትፎ እንዳላቸው የሚያሳየው ከሚስቶቻቸው ጋር ተመካክረው ሴቶቹ መከላከያውን እንዲወስዱ መፍቀዳቸው ነው፡፡ ወንዶች መከላከያው እንዳይወሰድ በሚያደርጉበት አካባቢ ሁሉ ሴቶች መከላከያውን ቢወስዱም እንኩዋን የሚጠቀሙት በጣም በችግር መሆኑን ብዙዎች ይመሰክራሉ፡፡ስለዚህ የወንዶቹ ተሳትፎ በአብዛኛው ለባለቤቶቻቸው ተጠቃሚነት ከማማከርና ከመፍቀድ የዘለለ ሆኖ አይታይም እንደ አቶ ጀማል ካሳው፡፡

አቶ ጀማል አክለውም “የወንዶች የቤተሰብ እቅድ ተሳትፎ ምን ይመስላል የሚለውን ስንመለከት በአገራችን በጣም ዝቅተኛ ከሚባል ደረጃ ላይ ያለ ነው፡፡ በእርግጥ በአለም አቀፍ ደረጃም ያለው መረጃ ዝቅተኛ መሆኑን የሚያመላክት ሲሆን ይህም የመነጨው በተለምዶ የተዋልዶ ጤና የሴቶች ጉዳይ ተደርጎ ስለሚታሰብ ነው፡፡ ወንዶች ብዙውን ጊዜ የቤተሰብ እቅድ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ግንዛቤው ስለሌላቸው ምን እንደሚጠበቅባቸው የማያውቁበት ሁኔታ አለ፡፡ ስለዚህ ወንዶቹ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ላይ ያላቸው ተሳትፎ አለ የሚባል አይደለም” ብለዋል፡፡

Read 3317 times Last modified on Saturday, 24 December 2011 08:22