Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 December 2011 07:48

የ2011 የዓለም ኮከብ ተጨዋች አሸናፊ ያከራክራል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ለ2011 የዓለም ኮከብ ተጨዋች ለሚሸለመው የወርቅ ኳስ አሸናፊነት ለቀረቡ 3 የመጨረሻ ዕጩዎች የሚሰጠው ግምት በዓለም ዙሪያ አከራካሪ ሆኗል፡፡ 3ቱ የመጨረሻዎቹ እጩዎች የባርሴሎናዎቹ ሊዮኔል ሜሲ እና ዣቪ ኧርናንዴዝ እንዲሁም የሪያል ማድሪዱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ናቸው፡፡ አሸናፊው ከ2 ሳምንት በኋላ በዙሪክ በሚከናወን ስነስርዓት ይታወቃል፡፡ በሌላ በኩል ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለ2ኛ ጊዜ በሚካሄደው የዓለም ኮከብ አሰልጣኝ ምርጫ የባርሴሎናው ፔፔ ጋር ዲዩላ፣ የሪያል ማድሪዱ ጆሴ ሞውሪንሆ እንዲሁም የማን.ዩናይትድ ሰር አሌክስ ፈርጉሠን በመጨረሻ ዕጩነት ቀርበዋል፡፡ ባርሴሎና በፔፔ ጋር ዲዮሳ እየሰለጠነ ባለፉት 4 ዓመታት ውስጥ 3 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን እና 3 ተከታታይ የላሊጋ የሻምፒዮናነት ድሎችን አግኝቷል፡፡

ባርሴሎና ከሳምንት በፊት የዓለም ክለቦች ሻምፒዮን ለመሆን ሲበቃም ዘንድሮም በዓለም እግር ኳስ የስፔን ክለቦች የበላይነትን ያረጋገጠ ክለብ አድርጐታል፡፡ በጋርዲዬላ ላለፉት 4 ዓመታት የሰለጠነው ባርሴሎና በአገር ውስጥና በአህጉራዊ ደረጃ 13 ትላልቅ ዋንጫዎችን ሰብስቧል፡፡ ይሄው ስኬት ፈረንሳዊውን የክለቡ አሰልጣኝ ፔፔ ጋርዲዮላ በመፎካከር የቀረቡትን 2 የኮከብ አሰልጣኝነት ዕጩ አሰልጣኞች ሊስተካከሉት  ስለሚያዳግት የዘንድሮው አሸናፊነት ቅድምያ ግምቱ ለፔፔ ጋርዲዬላ ይመስላል፡፡ በኮከብ ተጨዋች ምርጫው ዙሪያ ታላላቅ አሰልጣኞች፣ የቀድሞ ኮከብ ተጨዋቾች እና የአሁኑ ዘመን ምርጥ ተጨዋቾች የወርቅ ኳሱ ለማን ይገባል በሚለው ግምታቸው ከፍተኛ ክርክር ውስጥ ገብተዋል፡፡ ከእጩዎቹ አንዱ የሆነውና በ2008 የዓለም ኮከብ ተጨዋች የነበረው ፖርቱጋላዊው ክርስትያኖ ሮናልዶ በትዊተር አድራሻው ባሰፈረው ማስታወሻ በድጋሚ ከሦስቱ የመጨረሻ ዕጩዎች ተርታ መግባቱን  ታላቅ ክብር በማለት ገልፆታል፡፡ በ2009 እና በ2010 እ.ኤ.አ የፊፋ የዓለም ኮከብ ተጨዋች ለመሆን የበቃው ሊዩኔል ሜሲ ደግሞ ስለሽልማቱ ታላቅነትና ክብር ሲናገር 3ቴ ያሸነፈ ተጨዋች ተብሎ ከእነ ፕላቲኒ እና ቫንባስተን ጋር መጠራት ያጓጓኛል ብሏል፡፡ 3ኛው እጩ ዣቪ ኧርናንዴዝ በበኩሉ ለሶስተኛ ተከታታይ ዓመት በእጩነት በመቅረቡ ታላቅ ኩራት እንደሚሰማው ገልፆ ከልጅነቱ ጀምሮ የወርቅ ኳሱን የመሸለም ምኞት እንደነበረው ተናግሯል፡፡ በፊፋ የዓለም ኮከብ ተጨዋች ምርጫ ለ3ጊዜያት በማሸነፍ በታሪክ መዝገብ የሰፈሩት የቀድሞ ታላላቅ ተጨዋቾችም የወርቅ ኳሱን ማን እንደሚያሸንፍ በሰጡት ግምት ሁለቱ ወደ ሜሲ ሲያጋድሉ አንደኛው ለዣቪ ይገባዋል ብሏል፡፡ የ2011 ኮከብተጨዋች ሜሲ መሆኑን አልጠራጠርም ያለው ማርኮ ቫንባስተን   ሁሉንም ያሸነፈ ተጨዋች ቢሆንም ተጨማሪየማሸነፍ ፍላጐት ያለው በመሆኑ የወርቅ ኳሱ እንደሚገባው አስተያየት ሰጥቷል፡፡ አሁን የአውሮፓ እግር ኪስ ማህበር ፕሬዚዳንት የሆነው ሚሸል ፕላቲኒ ማንኛውም የክብር  ሪከርድ ሊሰብር እንደሚችል ሲናገር ሜሲ የሱን ስኬት ማለፍ እንደሚችል ገልጿል፡፡ ዮሃን ክሮይፍ በበኩሉ ሮናልዶና ሜሲ እጅግ በጣም ልዩ ብቃት ያላቸው ተጨዋቾች መሆናቸውን ቢገልጽም የዘንድሮውን ወርቅ ኳስ ለሌሎች ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ እና በኳስ ተጨዋችነቱ ባለው ታታሪነትና የበሰለ ስብዕና ዣቪ ኸርናንዴዝ መውሰድ አለበት ብሏል፡፡ ፖርቱጋላዊው ዩዝብዩ የወርቅ ኳሱ ለሚሴ እንደሚገባ እኔ ብቻ ሳልሬን እራሱ ክርስቲያኖ ሮናልዶም ያምንበታል ብሎ ሲናገር የሪያል ማድሪዱ ሪካርዶ ካካ ደግሞ በዘመናዊ እግር ኳስ ሁለገብ ተጨዋች ብሎ ለመሰከርለት ክርስቲያኖ ሮናልዶ የወርቅ ኳሱይገባዋል ብሏል፡፡ ዲያጐ አርማንዶ ማራዶና ሚሴ የሮናልዶ ተከታይ የሆነ ቀን ራሴው ስልክ ደውዬ የሌላ ሰው ተከታይ የምትሆነው ነው በፊፋ ምርጫ ብቻ ነው ብዬ እነግረዋለሁ ሲል ፈረንሳዊው የቀድሞ ተጨዋች ኢማኑዌል ፔቲት ከጆሲ ሞውሪንሆ ጋር ይመሳሰልብኛል ያለውን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለወርቅ ኳስ ሽልማት መርጦታል፡፡ የኢንተር ሚላኑ አብራሞቪች ድምጽ የምሰጠው ለሊዮኔል ሜሲ ነው ብሎ አስተያየት ሲሰጥ አብሬያቸውለምጫወተው ዣቪና ሜሲ አድናቄቴን እሰጣለሁ ሲል ሴስክ ፋብሪጋዝ ተናግሯል፡፡ በቀጣይ የውድድር ዘመናት ወደ ዓለም ኮከብ ተጨዋችነት መምጣቱ እንደማይቀር የሚገመተው ብራዚላዊው የሳንቶስ ክለብ ተጨዋች ፓብሎ ኔይማር በበኩሉ በኮከብ ተጨዋችነት የወርቅ ኳስ መሸለም ከዋንጫ ድል የማይተናነስ ክብር መሆኑን ሲገልጽ ሊዮኔል ሜሲ 1ኛ እንዲሁም ክርስቲያኖ ሮናልዶ 2ኛ ናቸው ብሏል፡፡ በፊፋ የ2011 የዓለም እግር ኳስ ክዋክብቶች ሌሎች የሽልማት ዘርፎች ከፍተኛ ትኩረት የሳበው በዓመቱ ምርጥ ጐል የፑሽካሽ አዋርድን ማን ያገኛል የሚለው ነው፡፡ ፊፋ በዚሁ ዘርፍ ለሚካሄደው ምርጫ በቅድሚያ 10 እጩዎችን አቅርቦ በድረገፁ ከ700ሺ በላይ ስፖርት አፍቃሪዎች ከሰጡት ድምጽ በኋላ የመጨረሻቸውን 3 እጩዎች ለይቶ አሳውቋል፡፡ በዚህ መሠረት ለፑሽካሽ አዋርድ የሊዮኔል ሜሲ፣ የዋይኔ ሩኒ እና የኔይማር ምርጥ ጐሎች ይወዳደራሉ፡፡ ከ50ሺ በላይ የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር አባላት በሚሰጡት ድምጽ ደግሞ የ2011 የፊፋ ምርጥ 11 ቡድን ተለይቶ ይታወቃል፡፡ ለዚሁ ምርጥ ቡድን ምርጫ ከቀረቡት 55 ዕጩዎች 12 ስፔናዊያን፣ 8 ብራዚላዊያን፣ 5 ጀርመናዊና 5 እንግሊዛዊያን ተጨዋቾች ተካትተዋል፡፡

 

 

 

 

Read 5960 times Last modified on Saturday, 24 December 2011 07:55