Saturday, 14 June 2014 11:23

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የሃጂ ጉዞ የስራ ስምምነት ከእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጋር ይፈራረማል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማህበር የሃጂ ጉዞ የስራ ስምምነት ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጋር ሊፈራረም እንደሆነ አስታወቀ፡፡ የፊታችን ሰኞ የሚደረገው የስራ ስምምነት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ውስጥ የሃጂ ጉዞ የስራ ትብብር ሲሆን ለዚሁ አገልግሎት የሚውል አዲስ የቁጠባ አገልግሎት መጀመርን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ባንኩ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

104 ያህል ቅርንጫፎችን በመክፈት በስፋት አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነ የገለፀው ባንኩ ባለፈው ታህሳስ ወር በአገራችን አዲስ የሆነውን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ከግል ባንኮች ቀድሞ በመጀመር የተገልጋዩን እርካታ ለመጨመር እየተጋ መሆኑን አስታውሷል፡፡ የፊታችን ሰኞ የሚፈረመው የሃጂ ጉዞ የስራ ትብብርና ለዚሁ ዓላማ የሚውለው አዲስ የቁጠባ ሂሳብ አገልግሎት መጀመርን የሚያበስረው የፊርማ ስነ-ስርዓት አዲስ አበባ ጦር ሃይሎች አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ውስጥ እንደሚከናወንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 1772 times