Saturday, 31 May 2014 14:21

20ኛው የዓለም ዋንጫ ልዩ ልዩ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ሻምፕዮኖቹ ታሪክ ይሰሩ ይሆን?
ብራዚል፣ አርጀንቲና፣ ጀርመን፣ ስፔን
የአለም ዋንጫ ባለቤት፣ የአውሮፓ ሻምፒዮን፣ የፊፋ ሰንጠረዥ ቁንጮ የሆኑት ስፔናዊያን፤ ዘንድሮ ታሪክ ይሰሩ ይሆን? እንደገና ዋንጫ ይዘው ወደ አገራቸው የሚመለሱ ከሆነ፤ 50 ዓመታት ያልታየ አዲስ ታሪክ ያስመዘግባሉ። የአለም ዋንጫን በተከታታይ ያሸነፈ ቡድን የለም - ከብራዚል በስተቀር - እ.ኤ.አ በ1962።
ለዋንጫ ቅድሚያ ግምት የተሰጣቸው ግን፣ ከሁሉም በፊት ለብራዚል ከዚያም ለአርጀንቲና ነው። በመቀጠል ለጀርመንና ለስፔን።

በስቴዲዬሞች ዝግጅት ብትዝረከረክም፣ ብራዚል 3.3 ሚሊዮን ቲኬቶችን ለመሸጥ ተስፋ አድርጋለች። የትኬቶቹ ዋጋ ይለያያል። ለመክፈቻው ውድድርየቲኬቶች ዋጋ 90 ዶላር (1800 ብር) ገደማ ነው።የአንዳንድ ጨዋታዎች ከዚህ ያንሳል። የመጨረሻው የዋንጫ ፍልሚያ ለመመልከት ግን 1ሺ ዶላር (20ሺ) ብር ገደማ ያስፈልጋል።
እንዲያም ሆኖ፣ ብራዚላዊያን በቅናሽ ትኬት እንዲገዙ ተፈቅዶላቸዋል - ለምሳሌ በ27 ዶላር (ከ500 ብር በላይ ነው)። የቲኬት ዋጋ ተወደደብን በሚል የተቃውሞ ረብሻ በየቦታው ተከስቶ እንደነበር ይታወሳል።



Hawk-Eye systemተብሎ የሚታወቀው ቴክኖሎጂ፤ አጀማመሩ ለጨዋታ የታሰበ አልነበረም። በአንድ በኩል እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ የሚወነጨፈውን ሚሳዬል በምን ያህል ፍጥነትና በየትኛው አቅጣጫ እየተጓዘ እንደሆነ ለመከታተልና ለመቆጣጠር ነው የተጀመረ ቴክኖሎጂ ነው - በወታደራዊ ምርምር። ዛሬ ዛሬ ጂፒኤስ ተብሎ ይታወቃል። ሃይለኛ የካሜራ አይን የተገጠመላቸው በርካታ ሳተላይቶች በምድራችን ዙሪያ ወደ ታች አፍጥጠወ ያንዣብባሉ፡፡ የማንኛውንም ነገር ምስል ይቀርፃሉ የሚሳዬልም ጭምር፡፡ ከምስራቅና ከምዕራብ፣ ከደቡብና ከሰሜን አቅጣጫውን ለማስላት እንዲሁም ከፍታውንም ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል መረጃ ያቀርባሉ፡፡ ይህንኑ ቴክኖሎጂ በትንሽ ቦታ ተግባራዊ ሲደረግ ነው - ለአንጐል ቀይ ህክምና ጠቃሚ የሆነው፡፡ ከኤክስሬይ ጋር በሚመሳሰል ዘዴ የአንጐልን ምስል የሚቀርፁ መሳሪያዎች በጭንቅላት ዙሪያ ይተከላሉ፡፡ እናም ከታች እስከ ላይ ከቀኝ እስከ ግራ ከፊት እስከ ኋላ ድረስ የአንጐልን ሙሉ ቅርጽ ለማየት ያስችላል፡፡


ዘመናዊ ስታዲዬም ግንባታ፣ የተራቀቀ ቀረፃና ስርጭት፣ ምርጥ ቲቪና ‘ሪፕሌይ’፣ ምቹ ታኬታና የሚያምር ማሊያ... እነዚህ ሁሉ የእግርኳስን ተወዳጅነት ያሻሻሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ቢሆኑም፤ ፊፋ ለቴክኖሎጂ ፍቅር የለውም። እንዲያውም ወደ ጠላትነት ያመዝናል። ዘንድሮ ግን፤ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር መራመድ ግድ ሆኖበታል።ዳኞች አሻሚ ነገር ሲገጥማቸው፣ የቪዲዮ ቀረፃ አይተው ቢፈርዱ ምናለበት? መስመር አልፎ ጎል የገባ ኳስና መስመር ያላለፈ ኳስ ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪ የሚሆንበት አጋጣሚ መኖሩ አይካድም። በቀላል የኤሌክትሮኒክስ ዘዴ መፍትሄ ቢበጅለትስ? በደቡብ አፍሪካ የ2010 የአለም ዋንጫ ሲካሄድ እነዚህን ቴክኖሎጂዎች መጠቀም ይቻል ነበር። ፊፋ በእጄ አላለም።ቴክኖሎጂዎቹን መጠቀም፣ በጨዋታዎች መሃል ልዩነት ያመጣል በማለት የተቃወሙት የፊፋ ፕሬዚዳንት ሰፕ ብላተር፤ የአለም ዋንጫ ውድድሮችና ተራ የወረዳ ጨዋታዎች በእኩል አይን መታየት አለባቸው ብለዋል። አየ ወግ! አንደኛ፤ የአለም ዋንጫና የወረዳ ውድድር በተፈጥሯቸው እኩል አይደሉም። ሁለተኛ፤ የጊዜ ጉዳይ እንጂ፣ ቴክኖሎጂው እስከ ወረዳና ቀበሌ መውረዱ የማይቀር ነው። ፊፋ ከአቋሙ ፍንክች የማለት ፍላጎት አልነበረውም። ነገር ግን፤ ለትክክለኛ ዳኝነት የሚረዳ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ባይውልም፤ የተሳሳተ ዳኝነትን የሚያጋልጥ ቴክኖሎጂን መከልከል አይቻልም። ከመዓት አቅጣጫ እየተቀረፀ የሚተላለፈው የቲቪ ስርጭት አብዛኞቹን የዳኝነት ስህተቶች ያጋልጣል። ለምሳሌ ባለፈው የአለም ዋንጫ የእንግሊዙ ላምፓርት በጀርመን ቡድን ላይ ያስገባት ጎል አላግባብ የተሻረችው በዳኝነት ስህተት ነው። እንዲህ አይነት ያፈጠጡ ስህተቶች ላይ የሚፈጠረው ውዝግብ ነው፤ በፊፋ ባለስልጣናት ላይ ጫና በማሳደር፤ ለቴክኖሎጂ እጅ የሰጡት።

Read 2133 times