ውድ እግዚአብሔር -
ባቢ ቢራ ጠጥቶ ሲመጣ አልወድም፡፡ አፉ መጥፎ መጥፎ ይሸታል፡፡ በዚያ ላይ ይጮህብኛል። አንተ ነህ ቢራ የፈጠርከው? ለምን?
ሳሚ - የ6 ዓመት ህፃን
ውድ እግዚአብሔር -
እሁድ እለት ሙሽሮቹ ቤተክርስትያን ውስጥ ሲሳሳሙ አየኋቸው፡፡ ፈቅደህላቸው ነው?
ሮዝ - የ5 ዓመት ህፃን
ውድ እግዚአብሔር -
ካንተ የተሻለ ለእግዚአብሔርነት የሚሆን ያለ አይመስለኝም፡፡ እንዲህ ያልኩት እግዚአብሔር ስለሆንክ አይደለም፡፡ የእውነቴን ነው፡፡
ቻርልስ - የ7 ዓመት ህፃን
ውድ እግዚአብሔር -
ዳይኖሰርን ባታጠፋው ኖሮ መኖር አንችልም ነበር፡፡ ትክክል ነው ያደረግኸው፡፡
ኤርሚ - የ7 ዓመት ህፃን
ውድ እግዚአብሔር -
በዓለም ላይ ያሉትን ሰዎች በሙሉ መውደድህ በጣም ያስደንቃል፡፡ እኛ ቤት አራት ሰዎች ብቻ ናቸው ያሉት፡፡ ሁሉንም መውደድ ግን አልቻልኩም፡፡
ናኒ - የ8 ዓመት ህፃን
ውድ እግዚአብሔር -
ሌሊት ሌሊት አስፈሪ ህልሞች አያለሁ። ከእነማሚ ጋር ልተኛ ስል አድገሃል ተባልኩ። አስፈሪ ህልሞች ከየት ነው የሚመጡት? ይሄ የሚመለከተው ሰይጣንን ነው አይደል?
ሔኖክ - የ6 ዓመት ህፃን
Published in
ህብረተሰብ