Saturday, 24 May 2014 14:35

“የእርግዝና መከላከያው ፎርጅድ ነው እንዴ?”

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ውድ የጤና አምድ አዘጋጅ:-
የሰላሳ ሁለት ዓመት ሴት ነኝ፡፡ ከስምንት ዓመት በፊት ከመሰረትኩት ትዳሬ ሶስት ልጆችን አፍርቻለሁ፡፡ በትምህርቴ እምብዛም ባለመግፋቴ፣ የእኔ የምለው ቋሚ ሥራ የለኝም፡፡ የቤተሰባችን መተዳደሪያ የባለቤቴ ወርሃዊ ደመወዝ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ኑሮአችን ብዙም የሚያወላዳ አይደለም፡፡ የቤተሰባችን ቁጥር ከዚህ በላይ እንዲጨምር ጨርሶ አንፈልግም፡፡ ስለዚህ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆንን አመታት አስቆጥረናል፡፡ የተለያዩ አይነት የወሊድ መከላከያ ዘዴዎችን ስጠቀምም ቆይቻለሁ፡፡ ባለፈው ታህሳስ ወር በአቅራቢያዬ ወደሚገኘው ጤና ጣቢያ ሄጄ፣ በክንድ ውስጥ የሚቀበረውን የእርግዝና መከላከያ መድኃኒት አስቀብሬ ወደ ቤቴ ተመለስኩ፡፡ ከሶስት ወራት በኋላ በተደጋጋሚ የህመም ስሜቶች ስለአጋጠሙኝ ወደ ሆስፒታል ሄጄ ተመረመርኩ፡፡ ውጤቱም የሶስት ወር ፅንስ በሆዴ መያዜን አረዳኝ፡፡ በእውነቱ ይሄ ለእኔ አምኜ ልቀበለው የማልችለው ትልቅ ዱብዕዳ ነበር፡፡ አስተማማኝነቱ በየሚዲያው የሚነገርለትን የወሊድ መከላከያ መድኃኒት ከትክክለኛው ቦታ፣ በትክክለኛው ጊዜዬ መውሰዴን አውቃለሁ፡፡ የወር አበባዬ መቅረቱን ተከትሎ ሁኔታው ስላሳሰበኝ ወደ ጤና ጣቢያው ሄጄ ጉዳዩን ነግሬአቸው ነበር። የባለሙያዎቹ ምላሽ ግን “የመከላከያው ባህርይ በአንዳንድ ሴቶች ላይ የወር አበባ እንዳይታይ ያደርጋል” የሚል ሆነ፡፡  መከላከያ መድኃኒቱ በክንዴ ውስጥ በተቀበረ በሦስተኛው ወር ግን ሐኪሞች መፀነሴን ነገሩኝ፡፡ አሁን ለዚህ ችግር ተጠያቂው ማነው? የወሊድ መከላከያ እየተባሉ የሚሰጡት መድሃኒቶች ፎርጅድ ናቸው ማለት ነው? አስተማማኙ የወሊድ መከላከያስ የትኛው ነው? እባካችሁ  ባለሙያ አነጋግራችሁ ምላሽ ስጡኝ፡፡
ሰናይት- ከአዲስ አበባ
ውድ በክንድ ውስጥ የሚቀበረውን የእርግዝና መከላከያ መድሃኒት ተጠቅመሽ ያለፍላጎትሽ ያረገዝሽ አንባቢያችን - በመጀመሪያ ድንገት ሳታስቢው ለተከሰተብሽ ችግር ከልብ ማዘናችንን ልንገልፅልሽ እንወዳለን፡፡ ግን እንዲህ ያሉ አጋጣሚዎች በየጊዜው ይከሰታሉ፡፡ የወሊድ መከላከያ መድኃኒቶች መቶ በመቶ እርግዝናን ሊከላከሉ ወይንም ሊያስቀሩ እንደማይችሉ የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
  በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የፅንስና የማህፀን ሃኪም የሆኑት ዶክተር አብርሃም ሲሳይ እንደሚሉት፤ ያልተፈለገ እርግዝና እንዳይፈጠር የሚያደርጉና አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ የተለያዩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ዘዴዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከልም መታቀብ፣ የወር አበባ መምጫ ጊዜን በመቁጠር መጠቀም፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የወንዱን የዘር ፍሬ ከሴቷ ብልት ውጪ ማፍሰስ፣ በኮንዶም መጠቀም፣ በየዕለቱ የሚወሰዱ ክኒኖችን መዋጥ፣ መርፌ፣ በክንድ ውስጥ የሚቀበር ሆርሞን፣ በማህፀን ውስጥ የሚቀመጥ ሉፕ መጠቀምና ማህፀን ማስቋጠር (ቲውባል ላይጌሽን) እንዲሁም ለወንዶች የዘር ቱቦን ማስቋጠር (ቫሌክቶሚ) ዋንኞቹ ናቸው። እነዚህን አማራጮች ማንኛዋም ዕድሜዋ ከ15-49 ዕድሜ ክልል ውስጥ ያለች ሴት እንደ ምርጫዋ ልትጠቀምበት ትችላለች፡፡ ሆኖም አንዳንድ ጊዜ ባለሙያዎች ከሴትየዋ የጤና ሁኔታ፣ ከዕድሜዋና ከአቋሟ ጋር ሊስማማ የሚችለውን የወሊድ መከላከያ አይነት ሊያዙ እንደሚችሉ ሃኪሙ ይገልፃሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት በአለማችን በአማራጭነት የቀረቡት በርካታ የወሊድ መከላከያ ዘዴዎች፣ የየራሳቸው የጎንዮሽ ጉዳትና የየራሳቸው ችግሮች እንዳሉባቸው የሚናገሩት ባለሙያው፤ ይህ ሁኔታም ከሰው ሰው እንደሚለያይና የጎንዮሽ ጉዳት መጠንም እንደሴቲቱ በሽታን የመቋቋም የተፈጥሮ አቅም ሊለያይ እንደሚችል ያስረዳሉ፡፡
ከወሊድ መከላከያ ዘዴዎች መካከል መቶ በመቶ አስተማማኝ ናቸው የሚባሉት ከግንኙነት መታቀብ፣ የማህፀን ቱቦን ማስቋጠር (ቲውባል ላይጌሽን)፣ የወንድ የዘር ቱቦ ማስቋጠር (ቫሎክቶሚ) ብቻ እንደሆኑ  የሚናገሩት ሃኪሙ፤ ሌሎቹ የመከላከያ ዘዴዎች መቶ በመቶ እርግዝናን ይከላከላሉ ማለት እንደማይቻል ጠቁመዋል፡፡ የእርግዝና መከላከያ መንገዶቹ ከ90-96 በመቶ እርግዝናን ይከላከላሉ ተብሎ እንደሚታመንና የመከላከያ ዘዴዎቹን የምንጠቀምበት ሁኔታና ጥንቃቄ የመከላከል ብቃቱን ከዚህም ሊቀንሱት እንደሚችሉ ተናግረዋል። “ኮንደምን ብንወስድ በአያያዝ ጉድለት ሊበላሽ፣ በአጠቃቀም ችግር ሊቀደድ ወይንም የመከላከል ብቃቱን ሊያጣ ይችላል፡፡ በየዕለቱ የሚወሰዱ ክኒኖችም ለአንድ ቀን እንኳን ቢዘነጉ የመከላከል አቅማቸው በእጅጉ ይቀንሳል” - ብለዋል ሃኪሙ፡፡
በክንድ ውስጥ የሚቀበረው የወሊድ መከላከያ አስተማማኝነታቸው ከ90-95 በመቶ ብቻ ከሆኑት የሚመደብ እንደሆነ የገለፁት ዶ/ር አብርሃም፤ መከላከያውን በትክክልና በአግባቡ ከወሰዱ 100 ሴቶች መካከል ከ5-10 የሚሆኑት እርግዝና ሊከሰትባቸው እንደሚችል ይናገራሉ፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች መድኃኒቶቹ ለብልሽት ሊጋለጡ ይችላሉ ያሉት ባለሙያው፤ ከአያያዝ ጉድለትና ከመጠቀሚያ ጊዜ ማለፍ የተነሳ፣ መከላከያዎቹ ከጥቅም ውጪ የሚሆኑባቸው ጊዜያት እንዳሉ ያስረዳሉ፡፡ ይሄኔ የታለመላቸውን አገልግሎት አይሰጡም ይላሉ - ሃኪሙ፡፡  የእርግዝና መከላከያ መድኃኒት እየተወሰደ ወይም ለተወሰኑ ጊዜያት የሚያገለግል ቋሚ የእርግዝና መከላከያ መድኃኒት በሰውነት ውስጥ እያለ በሚፈጠር እርግዝና ፅንሱ ጤናማ ሆኖ የመፈጠሩ ወይንም ጤናማ ሆኖ የመቀጠሉ ሁኔታ አጠራጣሪ እንደሆኑ የጠቆሙት ባለሙያው፤ የአካልና የአዕምሮ ችግር ያለባቸው ህፃናት ሊፈጠሩ አሊያም ፅንሱ ያለጊዜው ሊቋረጥ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
የትኛው የወሊድ መከላከያ ዘዴ በቋሚነት ወሊድን ያስቀራል? የትኛውስ ለምን ያህል ጊዜ ከመውለድ ሊታደገን ይችላል የሚለውን ጉዳይ በጥልቀት ማየትና የመረጡትን የወሊድ መከላከያ ከወሰዱ በኋላ መቶ በመቶ አስተማማኝ ለማድረግ ኮንደምን በተጨማሪነት መጠቀም እንደሚገባ ዶክተር አብርሃም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
 - ከአዲስ አበባ
በክንድ ውስጥ የሚቀበረውን የእርግዝና መከላከያ መድሃኒት ተጠቅመሽ ያለፍላጎትሽ ያረገዝሽ ውድ አንባቢያችን በመጀመሪያ ድንገት ሳታስቢው ለተከሰተብሽ ችግር ከልብ ማዘናችንን ልንገልፅልሽ እንወዳለን፡፡ ግን እንዲህ ያሉ አጋጣሚዎች ይከሰታሉ፡፡ የወሊድ መከላከያ መድኃኒቶች መቶ በመቶ እርግዝናን ሊከላከሉ ወይንም ሊያስቀሩ እንደማይችሉ የህክምና ባለሙያዎች በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የፅንስና የማህፀን ሃኪም የሆኑት ዶክተር አብርሃም ሲሳይን እንደሚሉት፤ ያልተፈለገ እርግዝና እንዳይፈጠር የሚያደርጉና አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ የተለያዩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ዘዴዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከልም መታቀብ፣ የወር አበባ መምጫ ጊዜን በመቁጠር መጠቀም፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የወንዱን የዘር ፍሬ ከሴቷ ብልት ውጪ ማፍሰስ፣ በኮንዶም መጠቀም፣ በየዕለቱ የሚወሰዱ ክኒኖችን መዋጥ፣ መርፌ፣ በክንድ ውስጥ የሚቀበር ሆርሞን፣ በማህፀን ውስጥ የሚቀመጥ ሉፕ መጠቀምና ማህፀን ማስቋጠር (ቲውባል ላይጌሽን) እንዲሁም ለወንዶች የዘር ቱቦን ማስቋጠር (ቫሌክቶሚ) የተባሉት ዋንኞቹ ናቸው። እነዚህን አማራጮች ማንኛዋም ዕድሜዋ ከ15-49 ዕድሜ ክልል ውስጥ ያለች ሴት እንደ ምርጫዋ ልትጠቀምበት ትችላለች፡፡ ሆኖም አንዳንድ ጊዜ ባለሙያዎች ከሴትየዋ የጤና ሁኔታ፣ ከዕድሜዋና ከአቋማ ጋር ሊስማማ የሚችለውን የወሊድ መከላከያ አይነት ሊያዙ እንደሚችሉ ሃኪሙ ይገልፃሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት በአለማችን በአማራጭነት የቀረቡት በርካታ የወሊድ መከላከያ ዘዴዎች የየራሳቸው የጎንዮሽ ጉዳትና የየራሳቸው ችግሮች እንዳሉባቸው የሚናገሩት ባለሙያው፤ ይህ ሁኔታም ከሰው ሰው እንደሚለያይና የጎንዮሽ ጉዳት መጠንም እንደሴቲቱ በሽታን የመቋቋም የተፈጥሮ አቋም ሊለያይ እንደሚችል ያስረዳሉ፡፡
ከወሊድ መከላከያ ዘዴዎች መካከል መቶ በመቶ አስተማማኝ ነው ሊባል የሚችለው ዘዴ ከግንኙነት መታቀብ፣ የማህፀን ቱቦን ማስቋጠር (ቲውባል ላይጌሽን)፣ የወንድ የዘር ቱቦ ማስቋጠር (ቫሎክቶሚ) ብቻ መሆናቸውን የሚናገሩት ሃኪሙ፤ ሌሎቹ የመከላከያ ዘዴዎች መቶ በመቶ እርግዝናን ይከላከላሉ ማለት እንደማይቻል ጠቁመዋል፡፡ የእርግዝና መከላከያ መንገዶቹ ከ90-96 በመቶ እርግዝናን ይከላከላሉ ተብሎ እንደሚታመንና ይህ አሃዝ የመከላከያ ዘዴዎቹን የምንጠቀምበት ሁኔታና ጥንቃቄ የመከላከል ብቃቱን ከዚህም ሊቀንሱት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ “ኮንደምን ብንወስድ በአያያዝ ጉድለት ሊበላሽ፣ በአጠቃቀም ችግር ሊቀደድ ወይንም የመከላከል ብቃቱን ሊያጣ ይችላል፡፡ በየዕለቱ የሚወሰዱ ክኒኖችም ለአንድ ቀን እንኳን ቢዘነጉ የመከላከል አቅማቸው በእጅጉ ይቀንሳል” - ብለዋል ሃኪሙ በምሳሌ ሲያስረዱ፡፡
በክንድ ውስጥ የሚቀበረው የወሊድ መከላከያ አስተማማኝነታቸው ከ90-95 በመቶ ብቻ ከሆኑት የሚመደብ እንደሆነ የገለፁት ዶ/ር አብርሃም፤ መከላከያውን በትክክልና በአግባቡ ከወሰዱ 100 ሴቶች መካከል ከ5-10 የሚሆኑት እርግዝና ሊከሰትባቸው እንደሚችል ይናገራሉ፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች መድኃኒቶቹ ለብልሽት ሊጋለጡ ይችላሉ ያሉት፡፡
ባለሙያው፤ ከአያያዝ ጉድለትና ከመጠቀሚያ ጊዜ ማለፍ የተነሳ፣ መከላከያዎቹ ከጥቅም ውጪ የሚሆኑባቸው ጊዜያቶች እንዳሉ ያስረዳሉ፡፡ ይሄን የታለመላቸውን አገልግሎት አይሰጡም ይላሉ - ሃኪሙ፡፡  የእርግዝና መከላከያ መድኃኒት እየተወሰደ ወይም ለተወሰኑ ጊዜያት የሚያገለግል ቋሚ የእርግዝና መከላከያ መድኃኒት በሰውነት ውስጥ እያለ በሚፈጠር እርግዝና ፅንሱ ጤናማ ሆኖ የመፈጠሩ ወይንም ጤናማ ሆኖ የመቀጠሉ ሁኔታ አጠራጣሪ እንደሆኑ የጠቆሙት ባለሙያው፤ የአካልና የአዕምሮ ችግር ያለባቸው ህፃናት ሊፈጠሩ አሊያም ፅንሱ ያለጊዜው ሊቋረጥ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
የትኛው የወሊድ መከላከያ ዘዴ በቋሚነት ወሊድን ያስቀራል የትኛውስ ለምን ያህል ጊዜ ከመወለድ ሊታደገን ይችላል፡፡ የሚለውን ጉዳይ በጥልቀት ማየትና የመረጡትን የወሊድ መከላከያ ከወሰዱ በኋላ መቶ በመቶ አስተማማኝ ለማድረግ ኮንደምን በተጨማሪነት መጠቀም እንደሚገባ ዶክተር አብርሃም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Read 7276 times