Saturday, 17 May 2014 15:24

የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ እየተጓተተ ነው

Written by 
Rate this item
(14 votes)

 ግንባታው የተጓተተው በገንዘብ እጥረትና በክፍያ መዘግየት ነው የቤቶች ልማት፤ የባጀት እጥረትም የጥራት ጉድለትም የለም ብሏል

           በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣ የባጀት እጥረትና የግንባታ ጥራት ችግር እንዳለባቸው ኮንትራክተሮች የገለፁ ሲሆን ሠራተኞችም ደሞዝ እስከ አራት ወር ይዘገይብናል ሲሉ ያማርራሉ፡፡ አሰሪው የቤቶች ልማት በበኩሉ፤ የግንባታ ጥራት እና የባጀት እጥረት እንደሌለበት ጠቁሞ፣ በአንዳንድ ተቋራጮች አቅም ማነስ የተነሳ የግንባታ መዘግየት መከሰቱን ገልጿል አቃቂ አካባቢ የሚገኘው የቂሊንጦ ሣይት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣ የባጀት እጥረትና የግንባታ ጥራት ችግር እንዳለባቸው ኮንትራክተሮች የገለፁ ሲሆን ሠራተኞችም ደሞዝ እስከ አራት ወር ይዘገይብናል ሲሉ ያማርራሉ፡፡ አሰሪው የቤቶች ልማት በበኩሉ፤ የግንባታ ጥራት እና የባጀት እጥረት እንደሌለበት ጠቁሞ ፤በአንዳንድ ተቋራጮች አቅም ማነስ የተነሳ የግንባታ መዘግየት መከሰቱን ገልጿል፡፡

ከተጀመረ አንድ አመት ከአምስት ወር ገደማ ባስቆጠረው የቂሊንጦ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሳይት፤ ለ7ሺህ ቤት ፈላጊዎች የሚሆኑ 290 ብሎኮች እየተገነቡበት ሲ ሆን ባ ለፈው ጥ ቅምት ወር የግንባታ ሂደቱን የጎበኙት ከንቲባ ድሪባ ኩማ፤አብዛኞቹ ቤቶች ዘንድሮ በጥር፣ ግንባታቸው ዘግየት ብሎ የተጀመሩት ደግሞ በሚያዚያ እንደሚጠናቀቁ ተናግረው ነበር። ሰሞኑን ሳይቱን የተመለከቱ ሪፖርተሮቻችን እንደገለፁት፤ አብዛኞቹ ቤቶች በብሎኬት እና ባልከን የግንባታ ሂደት ላይ ናቸው፡፡ በሳይቱ ላይ የሚሰሩ የህንፃ ተቋራጮች በሰጡት አስተያየት፤ “ከቤቶች ልማት ለስራ ማስኬጃ በየጊዜው የሚለቀቅልን በጀት ከእጅ ወደ አፍ ነው፤ በዚህም የተነሳ በ ገባነው ው ል መሰረት፤ ስራችንን አጠናቀን ማስረከብ አልቻልንም” ብለዋል፡፡ ሁሉም ተቋራጭ መኖርያ ቤትና ንብረቱን አስይዞ ወደ ስራው መግባቱን የጠቆሙት አንድ ኮንትራክተር፤ አሰሪው አካል የግንባታውን ሂደት እያጤነ ተገቢውን በጀት በወቅቱ ባለመልቀቁ፣ ለከፍተኛ ችግር እንደተጋለጡ ገልፀዋል፡፡

አንዳንድ የሙያ ባልደረቦቻቸው፤ በዚሁ ምክንያት ለኪሳራ ተዳርገው ሥራውን እንዳቋረጡም ኮንትራክተሩ ይናገራሉ፡፡ የቤቶቹ መሰረት እስኪወጣ ድረስ በጀት ቶሎ ቶሎ ይለቀቅላቸው እንደነበር የሚያስታውሱት ተቋራጩ፤ ወደ ማጠናቀቂያው ላይ ግን የበጀት አለቃቀቁ በቁጥ ቁጥ ከመሆኑም ባሻገር፣ ያለ ማስጠንቀቂያ ግንባታውን ነጥቆ ለሌላ አካል መስጠትን የመሳሰሉ ከውል ውጪ የሆኑ አሰራሮች መጀመራቸውን ይናገራሉ፡፡ ከቤቶች ልማት የሚለቀቀው ገንዘብ እኛ ከምንጠይቀው ከ6 በመቶ ብቻ ነው የሚሉት ተቋራጩ፤ ይሄም ለገንዘብ ችግር እንደዳረጋቸውና አብዛኛው ተቋራጭ ከራሱ ኪስ እያወጣ ብዙ ጉዳዮችን እንደሚሸፍን ይገልፃሉ፡፡ “ወር በደረሰ ቁጥር ተቋራጩ የሚከፍለው ደሞዝ እያጣ ከሰራተኛው ጋር የአይጥ እና ድመት ድብብቆሽ ይጫወታሉ፤ ይሄም አለመግባባት እየፈጠረ፣ አንዳንዶችን ለፀብ ሁሉ ይጋብዛል፤ ስራውን ለቀው የሚሄዱም ስላሉ ተቋራጩ በሰራተኛ እጦት ይቸገራል” ሲሉ ችግሮቻቸውን ያስረዳሉ -ተቆራጩ።

ችግሩ ግን የገንዘብ እጥረት ብቻ አይደለም - ተቋራጩ እንደሚሉት፡፡ ብሎኬት፣ ፕሪካስትና ሌሎች የግንባታ ግብአቶችን ራሱ የቤቶች ልማት እንደሚያቀርብ ጠቅሰው፣ አቅርቦቱ በቂ ካለመሆኑም በላይ የጥራቱ ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በተለይ ብሎኬቱ ገና ሲነኩት እንደሚፈረካከስ የሚገልፁት ተቋራጩ፤ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለመጥቀም ተብሎ የጥራት ቁጥጥር ያልተደረገለት ብሎኬት እየቀረበ ነው ሲሉ ያማርራሉ። ወደ ሥራ ለመግባት ኮንትራት ስንፈርም፣ ለግንባታ የሚያገለግሉ በቂ የውሃ፣ የመንገድ እና የኤሌክትሪክ አቅርቦት እንዳለ ተነግሮን ነው የሚሉት ሌላው የሳይቱ ህንፃ ተቋራጭ በበኩላቸው፤ እነዚህ ሁሉ አስፈላጊ ግብአቶች ግን እንደተባለው ተሟልተው ባለመገኘታቸው በስራው ላይ ከፍተኛ እንቅፋት እንደፈጠረባቸው ጠቁመዋል፡፡ የተስተካከለ መንገድ ባለመኖሩ ትንሽ ዝናብ ሲዘንብ አካባቢው ስለሚጨቀይ መንቀሳቀስ ¾cV’ < ›Ë”Ç የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ እየተጓተተ ነው አይቻልም የሚሉት እኒሁ ቅሬታ አቅራቢ ባለሙያ፤ አንዳንድ ተቋራጮች በራሳቸው ኪሳራ መንገዱን ለማስተካከል እንደሚሞክሩ ገልጸዋል፡ ፡

“የውሃ አቅርቦቱም ከሌላ አካባቢ በተሽከርካሪ የሚመጣ በመሆኑ፣ ለሁሉም ህንፃዎች በበቂ መጠን አይዳረስም፣ የጠብታ ያህል ነው” ብለዋል፡፡ የውሃ እጥረት በመኖሩም የህንፃዎቹ ግድግዳዎች ውሃ የሚጠጡት በጆክ እየተረጨ ነው ያሉት ተቋራጩ፤ ሰዎች ከገቡበት በኋላ ተሰነጣጥቀው ጉዳት እንዳይደርስ እሰጋለሁ ብለዋል። የግንባታ ግብአቶችን መርምሮ ማቅረብን ጨምሮ ሁሉም የስራ ኃላፊነቶች ለህንፃ ተቋራጮች ቢሰጥ ኖሮ፣ አሁን የሚነሱት የጥራት ጥያቄዎች ችግር አይሆኑም ነበር የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ ህንፃ ተቋራጩ ባላመነበት የግንባታ ቁሳቁስና የስራ ሂደት መመራቱ ተገቢ አይደለም ሲሉ ይተቻሉ፡፡ አንድ የህንፃ ተቋራጭ ለሰራተኛና ለግዢ ከሚያወጣው ማትረፍ ይጠበቅበታል ያሉት ተቋራጩ፤ አሰሪው አካል ባጀቱን አፍኖ በመያዙና ተገቢ የአከፋፈል ስርዓትን ባለመከተሉ ህንፃ ተቋራጩ የበይ ተመልካችና ተበዝባዥ ሆኗል ሲሉ ያማርራሉ። እኚህ ቅሬታ አቅራቢ ኮንትራት ከፈረሙ ጀምሮ የመጋዘን ጠባቂ ደሞዝ እና የጫኝ አውራጅ ተብሎ ከሚለቀቅላቸው በጀት ውጪ የቀረውን በራሳቸው እየሸፈኑ መቆየታቸውንም አክለው ገልፀዋል፡፡

ይህም መጀመሪያ ከአሰሪው አካል ጋር ከተዋዋሉት አጠቃላይ የገንዘብ መጠን አንፃር ቢሰላ ኪሳራ እንደሚያሳይ ጠቁመዋል፡፡ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ተቋራጮች፤ ቤት ንብረታቸውን አስይዘው ለስራ ማስኬጃ የተበደሩትን ገንዘብ እንኳ ሳይመልሱ “የስራ አፈፃፀማችሁ ደካማ ነው” ተብለው ግንባታው ወደ መጠናቀቁ ሲደርስ ሥራውን ይነጠቃሉ የሚሉት ሌላው የህንፃ ተቋራጭ፤ እሳቸውም ግንባታውን ካጠናቀቁ በኋላ፣ የማጠቃለያ ስራውን ጨምሮ በርና መስኮት መግጠሙን በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ወገኖች እንደተሠጠባቸው ይናገራሉ፡ ፡ ህንፃ ተቋራጩ ውሉን ከተፈራረመ በኋላ፣ በብዙ የስራ ሂደቶች ላይ የበይ ተመልካች ነው የሚሉት ቅሬታ አቅራቢው፤ ከግንባታ ስራው በከፍተኛ ደረጃ የሚጠቀሙት በጫኝና አውራጅነት የተደራጁ ወጣቶች እና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው ይላሉ፡፡

የቤቶች ልማት፣ ለህንፃው ግንባታ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ሊከፈለኝ ተስማምቷል፤ ነገር ግን እስካሁን ዘጠኝ መቶ ሺህ አምስት ብር ብቻ ነው የከፈለኝ ያሉት ሌላው ህንፃ ተቋራጭ፤ የገንዘብና የባጀት ጥያቄዎችን ስናነሣ ከፖለቲካ አንፃር እየተመነዘረ ‘ልማታዊ አይደላችሁም’ በሚል እንፈረጃለን በማለት የገቡበትን አጣብቂኝ ይገልፃሉ፡፡ በቤቶች ግንባታ ዘርፍ ሠፊ የስራ እድል መኖሩን ከጓደኞቹ ሰምቶ ከትውልድ ቀየው ደብረ ብርሃን ወደ አዲስ አበባ መምጣቱን የሚናገረው የ27 አመቱ ተስፋሁን፤ ምንም እንኳ የተነገረው የስራ እድል ቢኖርም የደሞዝ ክፍያ ከ2 እና ከ3 ወር በላይ እየዘገየ፣ ከቤት አከራዩ ጋር ንትርክ ውስጥ እየገባ በመቸገሩ በቅርቡ ወደ ትውልድ ቀዬው ለመመለስ መወሰኑን ጠቅሶ ቀደም ሲልም በተመሳሳይ ችግር ሥራቸውን ጥለው ወደ ትውልድ ቀዬአቸው የተመለሱ ጓደኞች እንዳሉት ጠቁሟል፡፡ በደሞዝ መዘግየት የተነሳ ብዙ ጊዜ ከአሠሪዎቹ ጋር መጋጨቱን የሚያስታውሰው ወጣቱ፤ አሠሪዎቹ ደሞዝ ሲጠየቁ በጀት እንዳልተለቀቀላቸው ለማስረዳት ይሞክራሉ ብሏል፡፡ ፕሮጀክቱን በኃላፊነት የሚመራው የአዲስ ከተማ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ቤቶች ግንባታ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ለማ፤ የቤቶቹ አጠቃላይ የግንባታ ሂደት 72 በመቶ መድረሱን ጠቁመው፣ የቤቶቹ ግንባታ ይጠናቀቃል ከተባለበት ጊዜ የዘገየው በተለያዩ ምክንያቶች ቢሆንም በዋናነት ግን በተቋራጮች ድክመት እና ከግብአት አቅርቦት ጋር በተያያዙ ችግሮች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የቤቶቹ ግንባታም ሆነ የግንባታ ግብአቶች ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገባቸው ነው የሚሉት ኃላፊው፤ አሰሪው አካል ብሎኬት፣ ብረትና ፕሪካስትን ጨምሮ 509 ዓይነት ግብአቶችን ለህንፃ ተቋራጩ እንደሚያቀርብ ጠቁመው፣ ተቋራጩ ደግሞ አሸዋ፣ ነጭ ድንጋይ እና ለሙሌት ስራ የሚውል ምርጥ አፈር ያቀርባል ብለዋል፡፡ ብሎኬት እና የተለያዩ የሲሚንቶ ውጤቶችን ጨምሮ ማንኛውም የግንባታ ግብአት በስርአቱ የጥራት ፍተሻ ተደርጎለት የማረጋገጫ ውጤት ሳይሰጠው ለግንባታ እንዲውል አይደረግም ያሉት ስራ አስኪያጁ፤ የጥራት ፍተሻ ማዕከል ውስጥ የጥራት ፍተሻ ተደርጎ ሰርተፍኬት ከተሰጠ በኋላ ነው ለተቋራጩ የሚቀርቡት ይላሉ። የብሎኬት ምርትን በተመለከተም 4ሺህ ያህል ብሎኬት ከተመረተ በኋላ እንደገና የጥራት ቁጥጥር ይደረጋል የሚሉት አቶ ሰለሞን፤ ከዚህ ባለፈም የአማካሪ ድርጅቶቹ የጥራት ተቆጣጣሪዎች በየእለቱ በየሳይቱ ተመድበው የምርት ጥራት ቁጥጥር ያደርጋሉ ብለዋል፡፡

ለግንባታ የሚውሉ የሲሚንቶ፣ የአሸዋ እና መሰል ግብአቶችን ውህደት መጠንና ጥራት ላይም ባለሙያዎች ከፍተኛ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ፤ግዢ ሲፈፀም ህግና መመሪያው በሚያዘው መሰረት ጥራታቸው ተፈትሾ እንደሚገዙ ጠቁመው ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊትም በአማካሪ ድርጅቱ ባለሙያዎች ፍተሻ ይደረግላቸዋል ብለዋል፡፡ በኔ እምነት በቤቶች ልማት የጥራት ደረጃ የሚገነባ ቤት አለ ለማለት እቸገራለሁ የሚሉት ስራ አስኪያጁ፤ እኛ ከምናቀርበው ግብአት ይልቅ ከፍተኛ የጥራት ችግር የሚያጋጥመው ለተቋራጮች በተተውት እንደ አሸዋና አፈር በመሳሰሉት ላይ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከውሃ አቅርቦት ጋር የተነሳውን ቅሬታ በተመለከተም አቶ ሰለሞን ሲመልሱ፤ ውሃ ከ4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በተሸከርካሪ እያመላለሰ የሚያቀርበው ቤቶች ልማት መሆኑን ጠቁመው፤ የውሃ አቅርቦት በሳይቱ ችግር ሆኖ አያውቅም፤ ውሃ ለጥራት ጉዳይ ተጠያቂ በማይሆንበት ደረጃ አድርሰናል ፣ነገር ግን አንዳንድ ተቋራጮች የውሃ መርጪያ ማሽኖች መጠቀም ሲገባቸው በጆግ ይጠቀማሉ፤ ይሄም ቢሆን በተገቢው መንገድ ስለመጠጣቱ በባለሙያዎች ቁጥጥር ይደረግበታል ብለዋል፡፡

ከበጀት እና ገንዘብ አቅርቦት ጋር ተያይዞ ለቀረበው ቅሬታ ሲመልሱም “ባለፈው 2006 የበጀት አመት ለሁለት ሳምንት ያህል ብቻ የበጀት መዘግየት አጋጥሞን ነበር፣ ከዚያ ውጭ የገንዘብ ችግር አጋጥሞን አያውቅም” ያሉት ሥራ አስኪያጁ፤ በኮንትራት ውሉና በፋይናንስ ስርአቱ መሰረት ተገቢውን ክፍያዎች ያለ እንከን እየፈፀምን ነው፤ ለዚህም ማስረጃ የሚሆኑ ሰነዶች አሉን ብለዋል። ሰራተኞች ደሞዝ አልተከፈለንም ብለው እኛ ጋ መጥተው ሮሮ ያሰማሉ፤ ችግሩም እንዳለ በሚገባ እናውቃለን የሚሉት ኃላፊው፤ ችግሩ የተፈጠረው ተቋራጮች የተከፈላቸውን ክፍያ ለሰራተኛ ደሞዝ ሳይከፍሉ ይዘው ስለሚሰወሩ ነው ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ ተቋራጩ ስራውን ስለሚነጠቅባቸው ሁኔታዎች ምላሽ የሰጡት ስራ አስኪያጁ፤ ለሁለት ጊዜያት ድክመቶች በማስጠንቀቂያ እንደሚታለፍና ከፍተኛ የአፈፃፀም ድክመት ያለባቸው ተጣርተው ለስራው ቅልጥፍና ሲባል እንደሚነጠቁ ገልፀዋል። በማንኛውም የቤት ግንባታ ላይ 40 በመቶ የስራ ድርሻ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተሰጠ መሆኑን አክለው የገለፁት ኃላፊው፤ በርና መስኮት እንዲሁም የጣራ ስራ ለነዚሁ አካላት የተተው መሆኑን ተቋራጮችም በሚገባ ያውቃሉ ብለዋል፡፡ ለተቋራጩ የግብአት አቅርቦት የተገደበበት ምክንያት ስራ አስኪያጅ ሲያስረዱ፤ ከፍተኛ ፕሮጀክት ስለሆነና ከ500 በላይ የግንባታ ግብአቶችን መጠቀም ስለሚያስፈልግ መሆኑን ጠቁመው፣

Read 7079 times