Saturday, 10 May 2014 12:28

ሰውን በመግደል ተወዳዳሪ ያልተገኘላት ፍጥረትና የቢል ጌትስ ጦርነት

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

እባብና ጊንጥ፣ ነብርና አንበሳ፣ ቀበሮና ጅብ አይስተካከሏትም - በነፍሰ ገዳይነቷ
ቱጃሩ ቢል ጌትስ፣ በትንኝ ላይ ያወጀው ጦርነት ከተሳካ ሚሊዮኖችን ከሞት ያድናል። በቴክኖሎጂ ፈጠራ ከአለማችን

ቁንጮ ሃብታሞች መካከል አንዱ ለመሆን የበቃው ቢል ጌትስ፣ በድሃ አገራት በተለይም በአፍሪካ ጤንነትና ትምህርት

እንዲስፋፋ በርካታ ቢሊዮን ዶላሮችን በመለገስ ዘመቻ ከጀመረ ቆይቷል። ከዘመቻዎቹ አንዱ ትንኝን ከምድረገፅ ማጥፋት

ነው። ለምን? የትንኝን ያህል ብዙ ሰዎችን የጨረሰ ሌላ ፍጥረት የለም።
እባብና አንበሳን፣ ጅብና ቀበሮን ... “እንደ ነብር” ብንፈራቸውም፤ ከትንኝ ጋር ሲነፃፀሩ የሚያስከትሉት አደጋ ትንሽ

ነው። ትንኝ፣ የወባ በሽታን በማሰራጨት በየአመቱ 200 ሚሊዮን ሰዎችን ለበሽታ ትዳርጋለች። የ600ሺ ሰዎችን ሕይወት

ትቀጥፋለች።
ከበረዷማው አንታርቲካ በስተቀር ትንኝ የሌለችበት የአለማችን አካባቢ የለም ማለት ይቻላል። አይነታቸው ብዙ ነው -

3500 ያህል የትንኝ ዝርያዎች አሉ። የመራባት ፍጥነታቸውም ለጉድ ነው። በተለይ፣ እርጥበትና ሙቀት በሚያገኙበት

ወቅት፣ ጠቅላላ የትንኞች ቁጥር በመቶ ትሪሊዮን የሚቆጠር ይሆናል - ለአንድ ሰው ከ15ሺ በላይ ትንኞች ይደርሱታል

ማለት ነው። ትንኝ፣ በቁጥር ብዛት ከጉንዳንና ከምስጥ በመቀጠል ተወዳዳሪ የላትም። ዘ ዊክ እንደዘገበው፣ በመላው

አለም ያሉ ምስጦችች 250 ትሪሊዮን ሲሆን፣ የጉንዳኖች ቁጥር የዚህን አራት እጥፍ ይሆናል - አንድ ኳድሪሊዮን

(ለሁሉም ሰው ብናከፋፍላቸው፣ ለእያንዳንዱ ሰው ከ140ሺ ጉንዳኖች በላይ ይደርሱታል)።

Read 3310 times