Monday, 27 January 2014 07:50

የጐንደር ላንድ ማርክ ሆቴል ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

በጐንደር ከተማ ጐህ ተራራን ተንተርሶ የተገነባው ላንድ ማርክ ሆቴል ባለፈው ሳምንት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ በጥምቀት ዋዜማ በድምቀት የተመረቀው ባለአራት ኮከብ ሆቴል፤ 75 ሚሊዮን ብር እንደወጣበት ባለቤቱ ኢንጂነር ነጋ ሀዲስ  ተናግረዋል፡፡
ሆቴሉ ለምረቃው ያዘጋጀውን ኬክ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ በረከት ስምኦን የቆረሱ ሲሆን ድምጻዊት ፍቅርአዲስ ነቅአጥበብ እና ድምጻዊ ተስፋዬ ታዬ እንግዶችን ሲያዝናኑ አምሽተዋል፡፡
ለ150 ሠራተኞች የሥራ እድል እንደፈጠረ የተነገረለት ላንድ ማርክ ሆቴል፤ 80 የመኝታ ክፍሎች፣ የስብሰባ አዳራሾች፣ ዘመናዊ ባርና ሬስቶራንቶች እንዲሁም የልጆች መጫወቻ ቦታ የተሟላለት እንደሆነ ታውቋል፡፡
ሆቴሉ ጉና ተራራ ላይ የጐንደር ከተማን በትኛውም አቅጣጫ አሽከርክሮ የሚያሳይ ልዩ የፈጠራ /ማማ/ እያስገነባ እንደሆነ ባለቤቱ ተናግረዋል፡፡ ሰዎች የሆቴሉን ግዙፍነት አይተው አቅማችን አይፈቅድም እያሉ መመለስ እንደሌለባቸው የገለጹት እንጂነር ነጋ፤ ሆቴሉ ሁሉም እንደ የአቅሙና ፍላጐቱ እንዲጠቀምበት ታልሞ የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

Read 2752 times