Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 03 December 2011 08:47

ዩሮ 2012 በጉጉት ይጠበቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከመንፈቅ በኋላ ፖላንድና ዩክሬን ለሚያስተናግዱት የአውሮፓ ዋንጫ ላለፉት 16 ቡድኖች ትናንት የምድብ ድልድል ወጣ፡፡በዩሮ 2012 የሚካፈሉት 16 ብሄራዊ ቡድኖች አዘጋጆቹን ፖላንድና ዩክሬን ጨምሮ ክሮሽያ፣ ቼክ ሪፖብሊክ፣ ዴንማርክ ፣እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ግሪክ ፣ታሊያን ፣ሆላንድ ፣ፖርቱጋል ፣ሪፖብሊክ ኦፍ አየርላንድ፣ ራሽያና ስዊድን ናቸው፡፡ ያለፈው አውሮፓ ዋንጫ እና የአለም ዋንጫ አሸናፊዋ ስፔንና በወጣቶች በተገነባ ቡድን አስደናቂ አቋም እያሳየች ያለችው ጀርመን ለዋንጫው ድል ልዩ ግምት ወስደዋል፡፡

የአውሮፓ ዋንጫው በርካታ ምርጥ ብሄራዊ ቡድኖችን በማሳተፉ በጉጉት እንዲጠበቅ ሲያደርገው በየብሄራዊ ቡድኖቹ የምርጥ ወጣት ተጨዋቾች መብዛት፤ የአህጉሪቱ ክለቦች መጠናከር እና በ19ኛው ዓለም ዋንጫ ያልተሳካላቸው እነ ጣልያን፤ፈረንሳይ ፤ ሆላንድ ፤እንግሊዝና ፖርቱጋል ውጤታቸውን ለማሻሻል በማተኮራቸው ከፍተኛ የፉክክር ድምቀት እንደሚኖረው ተገምቷል፡፡በአውሮፓ ዋንጫ ታሪክ 3 ጊዜ በማሸነፍ ጀርመን ክብረወሰን የያዘችው ሲሆን በስፔንና ፈረንሳይ እኩል 2 ግዜ አሸንፈዋል፡፡
ሁለቱ አዘጋጅ አገሮች እያንዳንዳቸው አራት ስታድዬሞችን አዘጋጅተዋል የመክፈቻውን ጨዋታ የሚያስተናግደው በፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶው የሚገኝ ብሄራዊ ስታድዬም ሲሆን ለፍፃሜው ደግሞ በዩክሬን መዲና ኪዬቭ የሚገኘው የኦሎምፒክ ስታድዬም እንደተመደበና በ681 ሚሊዮን ዶላር በድጋሚ እንደተሰራ ታውቋል፡፡
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ውድድሩ 1.7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደሚያስገኝ የገመተ ሲሆን በ231 አገራት በቴሌቪዥን ሲሰራጭ እስከ 5 ቢሊዮን ድምር የቲቪ ተመልካች ይኖረዋል ብሏል፡፡
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ለ16ቱ ብሔራዊ ቡድኖች ለተሳትፎ ብቻ ለእያንዳንዳቸው 8 ሚሊዮን ዩሮ የሚያከፋፍል ሲሆን በአጠቃላይ በሽልማትና በቦነስ ክፍያ የቀረበው 196 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡ ለሻምፒዮኑ ብሄራዊ ቡድን 7.5 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚበረከት ታውቋል፡፡
ትናንት የምድብ ድልድሉ በዩክሬኗ ከተማ ኪዬቭ ሲደረግ 70 የቲቪ ጣቢያዎች ስነስርአቱን በ150 አገራት አሰራጭተውታል፡፡ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በውድድሩ ለሚደረጉ 31 ግጥሚያዎች 1.4 ሚሊዮን ትኬቶች ለገበያ ያቀረበ ሲሆን 12 ሚሊዮን ስፖርት አፍቃሪዎች ለመግዛት አመልክተው ነበር፡፡

 

Read 3397 times Last modified on Saturday, 03 December 2011 08:51