Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 03 December 2011 08:49

ዋልያዎቹ ከሴካፋም ተሰናበቱ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በታንዛኒያ እየተካሄደ ባለው 35ኛው ሴካፋ ታስከር ሲኒዬር ቻሌንጅ ካፕ ላይ በምስራቅ አፍሪካ መገናኛ ብዙሐናት ለዋንጫ ግምት ተሰጥቶት የነበረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በምድብ ማጣሪያው ተሰናበተ፡፡ ትናንት በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ከማላዊ ጋር የተገናኘው ብሔራዊ ቡድኑ 1ለ1 አቻ መለያየቱ ለመውደቁ ምክንያት ሆኗል፡፡ በሻምፒዮናው ሁለቱ ተጋባዥ አገራት ዛምቢያና ማላዊ እንዲሁም ሩዋንዳ የየምድባቸው መሪ ሆነው ማለፋቸውን ሲያረጋግጡ ታንዛኒያ በምድብ 1 ሁለተኛ ሆና አልፋለች፡፡ በጥሎ ማለፍ ለመሳተፍ በቀሩት ቦታዎች ብሩንዲ፣ ዛንዚባር ኡጋንዳና ኬንያ ዛሬ የማጣሪያውን መገባደድ ይጠባበቃሉ፡፡

የሞት ምድብ በተባለው ምድብ 3 ከሱዳን፤ ኬንያ እና ማላዊ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በመጀመርያ ጨዋታው ከሱዳን ጋር 1 እኩል አቻ የተለያየ ሲሆን በሳምንቱ አጋማሽ ላይ በኬንያ ሁለት ለባዶ ተሸንፏል፡
በሌላ በኩል ዘንድሮ ለ3 ተከታታይ አመት የሴካፋ ዞን ሻምፒዮናን ስፖንሰር ያደረገው ሰርኔጂቲ ብሬዌሪስ የተባለው የምስራቅ አፍሪካ ትልቁ ቢራ ጠማቂ ኩባንያ በ2014 በብራዚል በሚደረገው 20ው አለም ዋንጫ የሴካፋ ዞን በአንድ ብሄራዊ ቡድን እንዲወከል ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡ ሰረንጄቲ ብሬወሪስ 35 ውን ሴካፋ ታስከር ሲኒዬር ቻሌንጅ ካፕ ስፖንሰር ያደረገው 450 ህ ዶላር በመለገስ ነው፡፡ የሴካፋ ምክር ቤት የዞኑን እግር ኳስ ለማሳደግ አባል አገራትና ስፖንሰሮች በታዳጊና ወታቶች ውድድሮች ላይ በቂ ትኩረትና ድጋፍ እንዲኖራቸው ያሳሰበ ሲሆን በቀጣይ አመት የዞኑን ውድድር ኬንያ እንድታዘጋጅ ወስኗል፡፡

 

Read 3809 times Last modified on Saturday, 03 December 2011 08:51