Saturday, 28 December 2013 10:47

የታክሲ ሹፌሮች፤ “ፌደራሎች ኤርፖርት ውስጥ አንበረከኩን” አሉ

Written by  ሰላም ገረመው
Rate this item
(0 votes)

•    ሻንጣዎችን ጭኖ የተሰወረ የታክሲ ሹፌር “ውለዱ” ተብለናል  

ሰሞኑን በቦሌ ኤርፖርት ፀጥታን በማስከበር ስራ ላይ በተሰማሩ ፌደራል ፖሊሶች እና የሚኒባስ ታክሲ ሾፌሮች መካከል

የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ዱላ ማምራቱን የተናገሩ ሹፌሮች፤ “ፌደራሎች ኤርፖርት ውስጥ አንበርክከው

ደብድበውናል” አሉ፡፡
ችግሩ የተፈጠረው ከዱባይ የመጣች ግለሰብን ሻንጣዎች ጭኖ በተሰወረ የሚኒባስ ታክሲ ሹፌር የተነሳ እንደሆነ የገለፁት

የሚኒባስ ሾፌሮች፤ የተሰወረውን ሹፌር “ውለዱ” በሚል የፌዴራል ፖሊሶች ኤርፖርት ውስጥ አንበርክከው

እንደደበደቧቸው ተናግረዋል፡፡ በሶስት ቀን ጊዜ ውስጥ የግለሰብ ላፕቶፕ፣ የመንግስት መስሪያ ቤት መኪና ትርፍ ጎማ

እና ሌሎች የተመላሽ ዜጎች ንብረቶች በመጥፋታቸውና  አቤቱታ በመብዛቱ ፌዴራሎቹ እርምጃውን ለመውሰድ

እንደተገደዱ ነግረውናል-ይላሉ ሹፌሮቹ፡፡
ከኤርፖርት አውቶቢስ ተራ የተመደበው የሚኒባስ ሹፌር ዳኜ አስቻለው እንደሚለው፤ ከሰኞ ጀምሮ በሚሰማው የዕቃ

መጥፋት አቤቱታ ምክንያት፣ የፌደራል ፖሊሶች ታክሲዎች ወደ ውስጥ እንዳይገቡ የከለከሉ ቢሆንም፤ ታፔላቸው

ኤርፖርት የሆኑ ታክሲዎች እየገቡ ሲሰሩ ነበር፤ ነገር ግን ሀሙስ እንደገና ላፕቶፕ በመጥፋቱ፣ ማታ ላይ ደግሞ ከዱባይ

የመጣች ሴት በርካታ ሻንጣዎችን የጫነ ታክሲ በመሰወሩ ምክንያት ፌደራል ፖሊሶች ሁሉንም ሾፌሮች በማንበርከክ

ደብድበዋቸዋል፡፡
የተደበደቡበትን ምክንያት ሲጠይቁም፤ “የእናንተ ጓደኞች ናቸው የወሰዱት፤ ካላመጣችኋቸው አንለቃችሁም” እንዳሏቸው

ዳኜ ገልፆ፤ በተለይ ተሳፋሪ አጥተው ሳይጭኑ ከግቢው የሚወጡ ሹፌሮችን በመለየት “ሳትጭን የወጣኸው ሰርቀህ ነው”

በማለት እያንበረከኩ በፖሊስ ዱላ እንደደበደቧቸው ገልጿል፡፡
በኤርፖርት ያገኘነውን የፌደራል ፖሊስ  ስለጉዳዩ ጠይቀነው፤ “እኛ ስለሌቦች ጉዳይ የምንናገረው የለም” በማለት ምላሽ

ሰጥቷል፡፡

Read 1316 times