Saturday, 28 December 2013 10:24

“ከትዝታ ጓዳ” እና “እንደወጡ የቀሩት ኢትዮጵያዊ” በድጋሚ ታተሙ

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(2 votes)

በዶ/ር ጌታቸው ተድላ የተፃፉትና ከዚህ በፊት ታትመው በነፃ የተከፋፈሉት “ከትዝታ ጓዳ” እና “እንደወጡ የቀሩት ኢትዮጵያዊ” መፃህፍቶች በድጋሚ ታትመው፣ ለሜቄዶንያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በስጦታ ተበረከቱ፡፡ ዶ/ር ጌታቸው በሜቄዶንያ በጐ ፈቃደኛ ሆነው እያገለገሉ ሲሆን ታህሳስ 13 ቀን 2006 ዓ.ም ማዕከሉ ባዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ መፃህፍቶቻቸውን ለሽያጭ አቅርበው ሁለቱ መፃህፍት ጥንድ ጥንዱ በ150 ብር ሲሸጡ ውለዋል፡፡ ገቢውም ለማዕከሉ መዋሉ ተገልጿል፡፡ “እንደወጡ የቀሩት ኢትዮጵያዊ” መፅሀፍ በወጣትነታቸው ከኢትዮጵያ ወጥተው በተለያዩ አለማት ሲዘዋወሩ ቆይተው በ85 ዓመታቸው ያረፉ ኢትዮጵያዊ ታሪክ ላይ ያጠነጥናል፡፡ “ከትዝታ ጓዳ” የተሰኘው መፅሀፍ ደግሞ ዶ/ር ጌታቸው በረጅም አመት የውጭ አገር ኑሯቸው ያጋጠሟቸውን አጠቃላይ የህይወት ገፅታ የቃኙበት እንደሆነ ታውቋል፡፡

Read 1557 times