የ 70 ወጣት ሰዓሊያንን ስራ ለተመልካች ይፋ ያደረገ የስዕል ኤግዚቢሽን ትላንት በ8 ሰዓት በጣይቱ ሆቴል ተከፈተ፡፡ “አርት ፌር” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው አውደርዕይ፤ 500 የሚጠጉ ስዕሎችን ያካተተ ሲሆን እስከ ነገ ማታ ድረስ ለተመልካች ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ቀደም ሲል እንዲህ ዓይነት የስዕል ባዛር በተለያዩ ስፍራዎች የተዘጋጀ ቢሆንም በጣይቱ ሆቴል ሲስተናገድ ግን የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡