Saturday, 07 December 2013 12:34

“ከአድማስ ፊት” ነገ ኪነጥበባዊ ዝግጅቱን ያቀርባል

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(0 votes)

በሻሸመኔ ከተማና አቅራቢያዋ ኪነጥበብ አፍቃሪዎች የተቋቋመው “ከአድማስ ፊት” የኪነጥበብ ማህበር 45ኛ ዝግጅቱን

ነገ ከቀኑ 7 ሰአት በሻሸመኔ የባህል አዳራሽ እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡ የዕለቱ የክብር እንግዳ በ “ትናንሽ ፀሐዮች” እማ

ጨቤን ሆና የምትተውነው አርቲስት ሰብለ ተፈራ ነች። በነገው ዝግጅት የጭውውት፣ የግጥም፣ የዘፈን፣ የመነባንብ

ሥራዎች ይቀርባሉ፡፡  ማሕበሩ ካሁን በኋላ በየወሩ በተለያዩ የጥበብ  ዘርፎች ውድድር እያካሄደ ለአሸናፊዎች የሚሸልም

ሲሆን የነገው ውድድርም በኮሜዲ ዘርፍ እንደሚሆን ማሕበሩ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡ ከ“አድማስ ፊት”

የተመሰረተበትን 6ኛ ዓመት በ50ኛ ዝግጅቱ በመጪው ሰኔ ለማክበር እየተዘጋጀ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

Read 1043 times