Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 19 November 2011 15:13

የእግር ኳስ ‹አፓርታይድ› እየተፈጠረ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሰሞኑን የፊፋው ፕሬዝዳንት ሴፕ ብላተር ‹በእግር ኳስ ዘረኝነት አለ ብዬ አላስብም፡፡ ቢኖር እንኳን በጨዋታ ላይ በተጨዋቾች መካከል የሚያጋጥም መሰዳደብ ጨዋታው ካለቀ በዃላ በመጨባበጥ ሊያበቃና ሊረሳ ይችላል፡፡› ብለው መናገራቸው አወዛጋቢ ሆነ፡፡ የብላተር አስተያየት ያበሳጫቸው የእንግሊዝ ሚዲያዎች የፊፋ ፕሬዝዳንት ከሆኑበት ስልጣናቸው እንዲነሱ ዘመቻ ሲጀምሩ በሌሎች የአውሮፓ አገራት በተለይ በስፔንና በጣሊያን አገር ያሉ ጋዜጦች ውዝግቡን ከቁብ ሳይቆጥሩት ቀርተዋል፡፡ ሴፕ ብላተር በእግር ኳስ ስፖርት ከዘረኝነት ጋር የተያያዙ ሁኔታዎች እንደሌሉ መቁጠራቸው አሳፋሪ ቸልተኝነት ነው በሚል የተቹ በርካታ ተጨዋቾች፤ የሚዲያ ዘገባዎችና የስፖርቱ ባለሙያዎች ናቸው፡፡

ፊፋና የአውሮፓ እግር ኳስ በእግር ኳስ ውድድሮች በሚያጋጥሙ የዘረኝነት ተግባራት ላይ ጥፋት የሰሩ ተጨዋቾችና የክለብ ደጋፊዎችን በማያዳግም ቅጣት አለማስተማራቸው ችግሩ እንደካንሰር ስፖርቱን ተጠናውቶ ሊገለው ይችላል የሚሉ ስጋቶችም በዝተዋል፡፡የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ባለው የንግድ እንቅስቃሴና ከመላው ዓለም የመጡ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች እንደመብዛታቸው በእግር ኳስ ስፖርት እያጋጠመ ያለውን ዘረኝነት ተጎጂ ያደርገዋል፡፡ በሊጉ የሚደረጉ ጨዋታዎች በቀጥታ የቴሌቭዠን ስርጭት ሲተላለፉ መላው የሰው ልጅ ስለሚታደማቸው ተጨዋቾች በሜዳ ላይ በሚያሳዩት ባህርይ ምን ያህሉን የዓለም ህዝብ ስሜት ሊጎዱ እንደሚችሉ መገንዘብ አለማቻላቸውን የሚወቅሱ ሚዲያዎች ጥቂት አይደሉም፡፡ዘረኝነት፣ አለመቻቻልና ማግለል በእግር ኳስ በሜዳ ውስጥና ከሜዳ ውጭ አሉታዊ ተጽእኖ በመፍጠር መቀጠላቸው ያሳስባል፡፡ ላለፉት 10 ዓመታት ፉትቦል አጌንስት

 

Read 2976 times Last modified on Saturday, 19 November 2011 15:16