Saturday, 19 November 2011 13:51

“ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል” ሥራ ሊጀምር ነው

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(0 votes)

የቻይና መንግስት በመላ አፍሪካ በራሱ ወጪ ከሚያስገነባቸው ሠላሳ ሆስፒታሎች ውስጥ አንዱ የሆነው ጥሩነሽ ቤጂንግ የኢትዮ-ቻይና ወዳጅነት ሆስፒታል ከአንድ ወር በኋላ ሥራ ይጀምራል፡፡ በ160 ሚሊዮን ብር አቃቂ አካባቢ የተሰራው እና 100 አልጋዎች ያሉት ባለ ሁለት ፎቅ ጠቅላላ ሆስፒታል ርክክብ ሰሞኑን የተከናወነ ሲሆን ሆስፒታሉን የሚያስተዳድረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ቢሮው 18 ኢትዮጵያውያን ዶክተሮችን ጨምሮ 400 የአስተዳደር እና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችን ለሆስፒታሉ እንደሚቀጥር ተገልጿል፡፡ 16 ቻይናውያን ዶክተሮች የሚኖሩት ሆስፒታሉ (በአቃቂ-ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ብቸኛው የመንግስት ሆስፒታል ሲሆን በአካባቢው እየተከሰተ ላለው ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ አፋጣኝ ሕክምና እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡ ¦

Read 5905 times Last modified on Tuesday, 22 November 2011 13:56