በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተውና በሊዛ ተሾመ የተደረሰው “ፍትህን በራሴ” ረዥም ልቦለድ መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ 248 ገፅ ያለው መፅሐፍ በሀገር ወስጥ 40.50 ብር፣ በውጭ ሀገራት ደግሞ 10 ዶላር እየተሸጠ ሲሆን ደሪሲዋ መታሰቢያቱን ለወሲብ ጥቃት ተጎጂዎች አድርጋለች፡፡ መፅሐፉ በኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት ማተሚያ ቤት የታተመ ሲሆን ደራሲዋ ካሁን ቀደም “አሜከላ ያደማው ፍቅር” የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ አብቅታለች፡፡