Saturday, 19 January 2013 14:48

"በዚህ ሳምንት" አስቂኝ የፍቅር ፊልም ይመረቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(1 Vote)

በእግር በፈረስ ፊልም ስራዎች" የተዘጋጀውና በደራሲና ዳይሬክተር አክሊሉ ገ/መድህን የተሰራው "በዚህ ሳምንት" የተሰኘ አስቂኝ የፍቅር ፊልም የፊታችን ረቡዕ በ11 ሰዓት በብሔራዊ ቴአትር እንደሚመረቅ ተገለፀ፡፡
ፊልሙ ጥር 19 ቀን 2005 ዓ.ም ደግሞ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በግል ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል ተብሏል፡፡ ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አንድ ዓመት ያህል ጊዜ እንደወሰደ የገለፁት አዘጋጆቹ፤ ከ610ሺ ብር በላይ ወጥቶበታል ብለዋል፡፡ ፊልሙ፤ በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ባጋጠመው የፍቅርና የሥራ መሰናክል ሙሉ ሳምንቱ ስለተቃወሰበት የስፖርት ጋዜጠኛና ስለሁለት አብሮ አደጐች እንደሚተርክ አዘጋጆቹ በላኩት መግለጫ ጠቁመዋል፡፡ 1 ሰዓት ከ33 ደቂቃ በሚፈጀው አስቂኝ የፍቅር ፊልም ላይ አክሊሉ ገ/መድህን፣ ህብረት ፈቃዱ፣ ፍቃዱ ከበደ ማሞ፣ አድማሱ ከበደ፣ ሚካኤል ታምሬ፣ አበበ ተምትም እና ሌሎችም ተሳትፈውበታል፡፡

Read 4226 times