አንድ ቀን ለአደን ሲወጣ ታዲያ ጠብመንጃውን አነሳሁ ብሎ ዣንጥላውን ይዞ ይወጣል፡፡ ገና ጫካ ውስጥ እንደገባም ከየት መጣ ሳይባል አንድ የተበሳጨ ድብ ፊትለፊቱ ገጭ ይልበታል፡፡ ከመቀፅበት ዣንጥላውን እንደጠመንጃ አስተካክሎ ድቡ ላይ ያነጣጥርበትና እጀታውን ይጫነዋል----ድቡ ወዲያው መሬት ላይ ጠብ ይላል” አላቸው ሃኪሙ፡፡
ሽማግሌውም “ይሄማ ሊሆን አይችልም! ድቡ ላይ የተኮሰው ሌላ ሰው መሆን አለበት!” አሉ - ጮክ ብለው፡፡
ሀኪሙም “የእርስዎም ነገር እኮ እንደዚያ መስሎኝ ነው” አላቸው፡፡