Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 05 January 2013 11:54

የኢትዮጵያ ደጋፊዎችና የትኬት ሽያጭ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

ከ31 ዓመታት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ የበቃው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከፍተኛ ድጋፍ በስታድዬም ያገኛሉ ተብለው ከሚጠበቁት ብሔራዊ ቡድኖች አንዱ ሆኗል፡፡ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ከ40ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ቡድኑን ለመደገፍ ከፍተኛ እንቅሰቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸው እየተገለፀ ይገኛል፡፡ ይህም ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከዛምቢያና ከአንጓላ ቀጥሎ በአፍሪካ ዋንጫው በከፍተኛ ደረጃ ድጋፍ ሊያገኙ ከሚችሉት አገራት ጋር ያሳልፋታል፡፡ የ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ኮሚቴ ከሳምንት በፊት ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት ኢትዮጵያ ለውድድሩ በቀረቡ ትኬቶች ግዢ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ናት፡፡

የአፍሪካ ዋንጫው አዘጋጅ ኮሚቴ የውድድሩን 500ሺ ትኬቶች ለመሸጥ አቅዶ እስከሰሞኑ ድረስ 300ሺ ሊሸጥ የበቃ ሲሆን የምድብ 3 ተፋላሚዎች የሆኑት ዛምቢያና ኢትዮጵያ ይመራሉ፡፡ ዛምቢያ በ50ሺ ትኬቶች ግዢ አንደኛ ስትሆን ኢትዮጵያ በ30ሺ ሁለተኛ፣ አልጀሪያ 15ሺ በመግባት 3ኛ ናቸው፡፡ አዘጋጇን ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ ሌሎቹ ተሳታፊ 13 አገራት በድምሩ 15ሺ ትኬት እንደገዙም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 7625 times