Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 05 January 2013 11:00

የካናዬ መልካም አባትነት ጥርጣሬ ፈጥሯል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ኪም ካርዴሽያን ከራፐር ካናዬ ዌስት የመጀመርያ ልጇን መፀነሷ እያነጋገረ ነው፡፡ ለስምንት ወራት በፍቅረኝነት ለቆዩት ሁለቱ ዝነኞች ግንኙነት መቀጠል የ12 ሳምንት እድሜ እንዳለው የተነገረው ፅንስ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብላል፡፡ ኪም ካርዴሽያን ከእርግዝናዋ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ዝና ያገኘችበት የሪያሊቲ ሾው እና የፋሽን ንግስትነቷ አደጋ ላይ ይወድቃል የሚል ስጋት እንዳለ ኤምቲቪ ሲጠቁም፤ “ዘ ሃፊንግተን ፖስት” በበኩሉ በአወዛጋቢነቱ የሚታወቀው ካናዬ ዌስት መልካም አባትነት ጥርጣሬ እንደፈጠረ ዘግቧል፡፡ ፎርብስ መፅሄት በቲቪ ኢንዱስትሪው ከፍተኛ ክፍያ በማግኘት በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጣት ኪም ካርዴሽያን፤ በፋሽን እና በኮስሞቲክስ ንግዷ 65 ሚሊዮን ዶላር ሃብት ማካበት እንደቻለች ታውቋል፡፡

ራፐር ካናዬ ዌስት በበኩሉ፤በሙዚቃ ፕሮዱዩሰርነት፤ በፋሽን ዲዛይነርነት እና በፊልም ተዋናይነት 90 ሚሊዮን ዶላር ሃብት አፍርቷል፡፡ ኪም “ኪፒንግ አፕ ዊዝ ዘ ካርዴሽያን” በተባለውና የመላው ቤተሰቧንና ዘመድ አዝማዷን የእለት ህይወት በሚያሳየው የቴሌቭዥን ሪያሊቲ ሾው ላይ በአንድ ክፍል 40ሺ ዶላር እየተከፈላት ትሰራለች፡፡
በ2012 ከቀረቡ ኮንሰርቶች የገቢ ደረጃ በቢልቦርድ የሙዚቃ የገበያ ሰንጠረዥ ተቀናቃኝ ያጣችው አሜሪካዊቷ ቴይለር ስዊፍት እስከ 10 ባለው ደረጃ ሳትገባ መቅረቷ አስገርሟል፡፡ 183 ኮንሰርቶችን በመላው ዓለም ለማቅረብ የተቻለበት የማይክል ጃክሰን ዘ ኢሞርታል ዎርልድ ቱር 147.3 በሚሊዮን ዶላር፤ በ67 ኮንሰርቶች ያቀረቡት ኮልድ ፕሌይ በ 147.3 በሚሊዮን ዶላር፤ ሌዲ ጋጋ በ65 ኮንሰርቶች 124.9 ሚሊዮን ዶላር፤ ኬኒ ቼዝኒ እና ቲም ማክግሩው በ23 ኮንሰርቶች 96.5 ሚሊዮን ዶላር፤ ቫን ሄለን በ46 ኮንሰርቶች 54.4 ሚሊዮን ዶላር፤ ጄይዚ እና ካናዬ ዌስት በ31 ኮንሰርቶች 47 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም አንድሬ ሬው በ99 ኮንሰርቶች 46.8 ሚሊዮን ዶላር በመላው ዓለም ገቢ በማድረግ እስከ 10 ያለውን ደረጃ እንደወሰዱ መፅሄቱ አመልክቷል፡፡

Read 4428 times

Latest from