የ20 ዓመት እድሜ ያለው ባንዱ የሮክ ሙዚቃ ስልትን በማነቃቃት እየተወደሰ ሲሆን ከዩ2፤ ሮሊንግ ስቶንና ቦን ጆቪ ተርታ መሰለፍ ጀምሯል፡፡
ከአልበሙ “ፓራዳይዝ” የተሰኘው የመጀመርያው ነጠላ ዜማ እንዲሁም “ቲር ድሮፕ” የተሰኘው ሌላ ዘፈን በሰሜን አሜሪካ ተወዳጅ ሆነዋል፡፡ የኮልድ ፕሌይ ባንድ የሪሃና ሙዚቃዎች አድናቂ በመሆኑ ከሷ ጋር ‹ፕሪንሰስ ኦፍ ቻይና› የሚል ዜማ መስራታቸውም ትኩረት አግኝቷል፡፡ “ቪቫ ላቪዳ” የተባለውን የኮልድ ፕሌይ 4ኛ አልበም ተሰርቶ ከሦስት ዓመት በፊት ለገበያ ሲበቃ ባንዱ በዓለም ዙርያ 50 ሚሊዮን ቅጂ ሸጦ ነበር፡፡ ተቀማጭነቱ በለንደን እንግሊዝ ውስጥ የሆነው ኮልድ ፕሌይ የሙዚቃ ባንድ በኦልተርኔቲቭ ሮክና በፖስት ብሪት ፖፕ የሙዚቃ ስልቶች ይታወቃል፡፡ ባንዱ ባለፉት 15 ዓመታት አራት የኤምቲቪ የሙዚቃ አዋርድ፤ 7 የግራሚ ሽልማቶችን ሰብስቧል፡፡