አራት የግራሚ ሽልማቶችን የወሰደችው ቴይለር ስዊፍት፤ “ስፒክ ናው” የተባለው አልበሟ ለ5 ጊዜያት በሽያጭ የፕላኒቲኒዬም ደረጃ ያገኘ ከመሆኑም በላይ ዘንድሮ በአሜሪካ ከፍተኛ ሽያጭ ካገኙ አልበሞች ግንባር ቀደም ሆኖላታል፡፡ ከዚሁ ዓልበም ላይ 14 ዘፈኖችዋ በቢልቦርድ 100 ትኩስ ዘፈኖች ደረጃ ውስጥ ገብተዋል፡፡ የቢልቦርድ ዘገባ እንደገለፀው፤ ቴይለር ስዊፊት በዓለም ዙሪያ 20 ሚሊዮን የአልበም ቅጂዎች የሸጠች ሲሆን 40 ሚሊዮን ዘፈኖቿ ከኢንተርኔት መጫናቸውንም አመልክቷል፡፡