Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 15 October 2011 13:07

ለ10ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ምዝገባው በ9 ቀን አለቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከ6 ሳምንታት በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ ጎዳናዎች ላይ ለሚካሄደውና 10ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሲካሄድ የነበረው ምዝገባ በ9 ቀናት አለቀ፡፡ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጆች በ10 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድሩ ላይ ተሳታፊ ለመሆን 36ሺ ስፖርተኞች በ9 ቀናት ጊዜ ውስጥ መዝግበው መጨረሳቸውን እንደረኩበት ገልፀዋል፡፡ ለዚሁ ፈጣን የምዝገባ ሂደት የግልና የመንግስት ተቋማት ለሰራተኞቻቸው በአማካይ እስከ 1ሺ ቲሸርት በመግዛት ያረጉት ርብርብ፤ በፖስታቤት በኩል በመላክ እስከ 15ሺ ቲሸርት መሸጡና በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ያለው ፍላጎት መጨመር ምክንያት እንደሚሆንም አስረድተዋል፡፡

ታላቁ ሩጫ ከ10 ዓመት በፊት ሲጀመር የመሮጫ ቲሸርቱን ለመሸጥ አንድ ወርና ከዚያም በላይ ጊዜ ይወስድ እንደነበር የሚያስታውሱት የውድድሩ አዘጋጆች በየዓመቱ ይሄው የምዝገባ ጊዜ እየቀነሰ መሄዱን አመልክተዋል፡፡ በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች በ10 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫው በብቃት ለመሳተፍ ከመካሄጃው ቀን 6 ሳምንት ቀደም ብሎ መዘጋጀት የሚኖርባቸው ሲሆን ከዛሬ መጀመር አለባቸው፡፡ ጀታላቁ ሩጫ በኢትዮያ ኦፊሴላዊ ድረገፅ ላይ በቀረቡ መረጃዎች ለልምምዳቸው ጠቃሚ ምክር እንደሚያገኙ ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል ታላቁ ሩጫ በኢትዮያ ከተባበሩት መንግስታት ጋር በመተባበር” በ2011 ለህፃናት እሮጣለሁ” በሚል መርህ በሚያደርገው ዘመቻ 1 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ አቅዶ እስካሁን 509ሺ ብር ማግኘቱ ታውቋል፡፡ ይህንኑ የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻ ለ6 አመታት ከ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫው ጋር በማያያዝ አከናውኖ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ለግብረሰናይ ድርጅቶች ለግሷል፡፡ አምና በ9ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮፕያ በተመሳሳይ ዘመቻ 808778 ብር ተሰብስቦ ለሜሪ ጆይና ለአበበች ጎበና የበጎ አድራጎት ተቋማት መበርከቱ ይታወሳል፡፡በተያያዘ ዜና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከኮካኮላ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው የ7 ኪሎሜትር ተከታታይ የጐዳና ላይ ሩጫ 2ኛው ሂደት በነገው እለት ይቀጥላል፡፡ 3ሺ ተሳታፊዎች ያሉት ይህ ውድድር ማይክሮቺፕ በተገጠመላቸው የመሮጫ ጫማዎች መደረጉ ልዩ ያደርገዋል፡፡ በመጀመርያው ውድድር ተሳታፊ የሆኑ አትሌቶች 7 ኪሎ ሜትሩን የገቡበትን ሰዓት ከታላቁ ሩጫ በኢትዮያ ኦፊሴላዊ ድረገፅ በማግኘት በነገው ተሳትፎ መቅረብ መቻላቸው የተሻለ ሰዓት ለማስመዝገብ ይረዳቸዋል ብለዋል የውድድሩ አዘጋጆች፡፡

 

Read 5359 times Last modified on Saturday, 15 October 2011 13:08